እግዚአብሔር ብዙ ችሎታዎችን ሰጥቶዎታል። የእግዚአብሔር ስጦታ በውስጥዎ አለ! ይህ ስጦታ በውስጥዎ ሳይሠራበትና ተኝቶ እንዲቀር አይፍቀዱ። ዓለም እነዚህ ስጦታዎች በእርስዎ ውስጥ ተገልጠው እስኪታዩ እየተጠባበቀ መሆኑን ያስታውሱ። በውስጥዎ ያሉትን እነዚህን ስጦታዎች ማንቀሳቀስና እንዲገለጡ ማድረግ ይኖርብዎታል። ብዙ ሰዎች ይድናሉ! የእግዚአብሔር ስጦታ በእርስዎ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተቀስቅሶ ወደ ተግባር ሲገባ ብዙ ሰዎች ይፈወሳሉ፣ ብዙዎችም ይባረካሉ!
በዙሪያዎም እንዲሁ ብዙ ተሰጥኦ ያላቸው ሰዎች አሉ። እንደ አለመታደል ሆኖ ብዙዎቹ ስጦታቸውን ሳይጠቀሙበት ወይም ምን ማድረግ እንደሚችሉ ሳያሳዩ ይኖራሉ፣ ይሞታሉም። ብዙ ተሰጥኦ ያላቸው ሰዎች ስጦታቸውን ሳይቀሰቅሱ ሕይወታቸውን ይገፋሉ። የእነርሱን ስጦታ ካነቃቁት በዙሪያዎ እጅግ የተዋጣላቸው ሰዎች እንዳሉ ይረዳሉ። ይህ ውድ መጽሐፍ የእርስዎንና በዙሪያዎ ያሉትን ሰዎች ስጦታ እንዴት ማንቃት እንደሚችሉ የሚያስተምር ነው።
በደራሲውና በፓስተሩ ዳግ ሂዋርድ-ሚልስ የተዘጋጀውን ይህን ጥልቅ ሥራ ካነበቡ በኋላ ለዓለም አስገራሚ ሰው ይሆናሉ! ብዙዎች በእርስዎ ውስጥ ባለው የእግዚአብሔር ስጦታ ታላቅነት ይደነቃሉ። እርስዎ የተቀቡ ነዎት! በእግዚአብሔር የተጠሩ ነዎት! የእግዚአብሔር ስጦታ አለዎት! ብዙ ነገሮች በውስጥዎ ተኝተው ይገኛሉ። ዓለም የመንፈስ ቅዱስን ኃይል እንዲገልጡ ይጠብቅዎታል። የእግዚአብሔርን ስጦታ ያንቁ!

Reviews
There are no reviews yet.