የማይጠማውን ሰው እንዲጠጣ ማድረግ በጣም አስቸጋሪ ነው ። መጠጣት እንዲችል ጥማት መኖር አለበት ። እስከ ሞት ድረስ የታመነ መሆን ማለት በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ተስፋ አለመቁረጥ ማለት ነው! እስከ ሞት ድረስ የታመነ መሆን ማለት እስከ ሞት ድረስ ታማኝ፣ ጽኑ፣ ያው፣ የማይናወጥና የማይለወጥ መሆን ማለት ነው ።
ጌታን በማገልገልህ ስትቀጥል፣ በእርግጥ መሰናከል፣ መውደቅና አለመታመን የሚያጋጥሙህ አጋጣሚዎች ይመጣሉ ። ኢየሱስ በማቴዎስ 18:7 ላይ እንዲህ ሲል ያስጠነቅቀናል፦ “…መሰናክል ሳይመጣ አይቀርምና፤…” ብዙ ሰዎች ሩጫቸውን ይሮጣሉ፤ ነገር ግን በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት በድንገት ወድቀው መሬት ላይ የሚፈጥጡበት ደረጃ ላይ ይደርሳሉ ።
የመሰናከያ ድንጋዮች ወደሚጠበቀው ፍጻሜ መድረስን የማይቻል ሊያደርጉት ይችላሉ ። አንተም መከላከል ያለብህ ይህንን ነው! መሬት ላይ እንዳትወድቅና ከሩጫው ውጭ እንዳትሆን ተጠንቀቅ ። እነዚህ የአዳኛችን መመዘኛዎች ናቸው፤ በእነርሱም ማመንህና በተግባር ላይ ማዋልህ አስፈላጊ ነው ። በታዋቂው ደራሲ ዳግ ሂዋርድ-ሚልስ የተጻፈው ይህ ወቅታዊ መጽሐፍ እስከ መጨረሻው ድረስ በታማኝነት እንድትጸና ያነቃቃሃል ።

Reviews
There are no reviews yet.