እግዚአብሔር የሰጠውን ተሰጥኦ ለመንግሥቱ የማይጠቀም ማንኛውም ሰው፣ ጣዕሙን እንዳጣ ጨው ነው። ፍሬ አልባ አገልጋዮች ጣዕሙን ላጣ ጨው ጥሩ ምሳሌዎች ናቸው። ኢየሱስም የማይጠቅም አገልጋይ ለምንም እንደማይረባ ተናግሯል።
ጨው መኖሩ እንዲታወቅ ማድረግ አስፈላጊ ነው። በምግብህ ውስጥ ጨው ሊኖር ይችላል፤ ነገር ግን ተፅዕኖ እንዲኖረው በቂ መሆን አለበት። እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፣ ስለዚህ በዚህች ምድር ላይ መኖራችሁ እንዲታወቅ ማድረግ አለባችሁ! ለመንግሥቱ ለምንም የማትረቡ ናችሁ?
ስለ ጨውና ስለ ምስጢራዊ ተፅዕኖው እንዲሁም ለእግዚአብሔር መንግሥት ስላለው ትንቢታዊ ጠቀሜታ የሚናገረው ይህ የትንቢት መጽሐፍ፣ ለእግዚአብሔር ስላላችሁ ጠቃሚነት ወይም ጥቅም አልባነት በጥልቀት እንድታሰላስሉ ያደርጋችኋል። በሕይወታችን ውስጥ ያለውን የጨው ሚና በመመርመርና በመረዳት፣ ለምንም የማይረባ መሆን ምን ማለት እንደሆነ በዚህ ቀስቃሽ መጽሐፍ ውስጥ ትማራላችሁ። ለምንም የማትረቡ አያድርጋችሁ!

Reviews
There are no reviews yet.