ክብር እያንዳንዱ ሰው ሊያውቀው የሚገባ ጠቃሚ ነገር ነው። ክብርን መስጠት የመጽሐፍ ቅዱስ ትእዛዝ ነው። ከእግዚአብሔር ጋር ባለዎት ግንኙነት ውስጥ ክብር በጣም አስፈላጊ ነው። ከነቢይዎ፣ ከፓስተርዎ፣ ከባልዎ እና ከሌሎች የሥልጣን አካላት ጋር ባለዎት ግንኙነት ውስጥም ክብር ትልቅ ቦታ አለው። ክብር ለሚገባው ሰው ክብር ካልሰጡ፣ ከተወሰኑ ሰዎች ጋር ሊኖርዎት የሚገባው ትክክለኛ ግንኙነት ሊኖራችሁ አይችልም።
ይህ ለሕይወት መመሪያ የሚሆን መጽሐፍ ነው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ለአንድ ሰው እንዴት ክብር መስጠት እንደሚቻል፣ የአለመከበር ምልክቶች፣ የክብር ዋጋ እና ሌሎች ብዙ ነገሮችን ይማራሉ። ይህ መጽሐፍ አስፈላጊ የሆኑ ግንኙነቶችዎን ለመጠበቅ የሚረዱ ቁልፎችን ይዟል። በክብር ረገድ ጎድለው እንዳይገኙ ምኞቴ ነው!

Reviews
There are no reviews yet.