ከብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት የምስክር ወረቀቶች ክምችት በላይ ለአገልግሎት የሚያስፈልግ ሌላ ነገር አለ። መካንነት (Barrenness) በተፈጥሮም ሆነ በአገልግሎት ውስጥ የሚከሰት አስከፊ፣ አስጨናቂ እና አውዳሚ ችግር ነው። በአገልግሎት ውስጥ የሚታይ መካንነት ለብዙዎቻችን መጋቢዎች (pastors) ተስፋ መቁረጥ፣ ቅሬታ እና ግራ መጋባት ምክንያት ነው። ብዙ መጋቢዎች በአገልግሎታቸው መካን ስለሆኑ በተስፋ መቁረጥ እና በግራ መጋባት ምክንያት ከሩጫው ይወጣሉ።
በዘመናዊቷ የክርስቲያን ቤተክርስቲያን ውስጥ እውነተኛ ፍሬ ለማጣት ምክንያቱ መካንነት ነው። ብዙ እንቅስቃሴዎች እና ብዙ ፕሮግራሞች አሉ፤ ነገር ግን ፍሬው ጥቂት ነው ወይም ጨርሶ የለም። እግዚአብሔር ፍሬያማ እንድንሆን ይፈልጋል። እግዚአብሔር በአገልግሎት እንድንሰፋ ይፈልጋል።
ፍሬያማ ለመሆን መካንነት በትክክል ምን እንደሆነ መረዳት አለብዎት። መካንነት እግዚአብሔር በአገልግሎትዎ ውስጥ ሊፈታው የሚፈልገው ችግር ነው። በዳግ ሂዋርድ-ሚልስ (Dag Heward-Mills) የተዘጋጀው ይህ ወቅታዊ መጽሐፍ፣ በአገልግሎትዎ ውስጥ ካለ መካንነት እንዲወጡ ይረዳዎታል። የመካንነት መንፈስ ሲወገድ፣ ወደ ፍሬያማነት ይሸጋገራሉ።
ዛሬ ከመካንነት እየወጡ ነው!

Reviews
There are no reviews yet.