ዳግሂዋርድሚልስ፣በርካታተፈላጊመጽሐፍየጻፉናከእነዚሁምውስጥ“ታማኝነትናታማኝአለመሆን” የተባለውበዓለምላይታዋቂበሆነውንመጽሐፋቸውይታወቃሉ።በአሁኑጊዜዩናይትድዲኖምኔሽንኦርጂኔትድፍሮምዘላይትሃውስግሩፕኦፍቸርች(United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches) ተብሎየሚጠራውቤተክርስቲያንመስራችናቸው፡፡በአሁኑጊዜሶስትሺህቤተክርስቲያኖችአሉት።
ዳግሂዋርድሚልስ፣በዓለማቀፍደረጃወንጌላዊሲሆኑ“ፈዋሹኢየሱስክሩሴድ(HEALING JESUS CRUSADE) ” በተሰኘውእናበአለምዙሪያበተለያዩኮንፈረንሶችላይበአገልግሎታቸውይታወቃሉ፡፡ይበልጥመረጃከፈለጉድህረገጻቸውንይጎብኙ፣www.daghewardmills.org.

  • ይህ የሚበረታታ መጽሐፍ ነው፡፡ መጋቢ የሆነው ቢሾፕ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ ለምንና እንዴት የመጋቢነትህን አገልግሎት ወጤታማ ማድረግ እንደሚቻል ያስረዳል።

  • የእግዚአብሔር መንጋ እረኛ ከሆንህ፣ በዚህ በሚገባ በተጤነ ሥራ በከፍተኛ ሁኔታ እገዛ ታገኛለህ፡፡ እነኚህ ገፆች ዝርዝር እና በጥንቃቄ የተመረጡ መመሪያዎችን ይዘዋል፡፡ ቢሾፕ ዳግ ሂዋርድ-ሚልስ ከሠላሳ ዓመታት በላይ ካካበቱት የእረኝነት ልምድ በመነሳት በአገልግሎት ሥራ ውስጥ ያሉ ተግባራዊ ዕይታዎችን ያካፍላሉ፡፡ የእግዚአብሔር መንጋ እረኛ የመሆን መሻት ካለህ፣ ይህ ስትፈልገው የነበረ ምሪት ሰጭ መጽሐፍ ነው፡፡

  • እረኛ የሚለውን ቃል ስንሰማ በሃሳባችን የሚመጣው « በግ « ነው። በጎች በእረኞች የሚያስፈልጋቸው ጥገኛ የሆኑ ፍጡሮች ናቸው። እረኛ በጎችን የሚንከባከብና የሚወድ እነርሱንም የሚመራ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር እኛ የእርሱ የማሰማርያው በጎችን እንደሆንን ያሳየናል። ኢየሱስ ደቀመዝሙሩን ጴጥሮስን ለጌታ ፍቅር ማረጋገጫ እንዲሆን በጎቼን መግብልኝ ብሎታል። እረኛ መሆን ትልቅ ሥራ ነው። በእግዚአብሔር ግብረኃይል ውስጥ በመካተት በጎችን መጠበቅ ትልቅ መታደል ነው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ የእግዚአብሔርን ህዝብ የመጠበቅ ታላቅ ሥራ ውስጥ እንዴት አድርገን መግባት እንዳለብን ይጋብዘናል፣ይገፋፋናል፣ያሳየናል። ካማረው

  • እግዚአብሔርን መከተል አስደሳች የአዳዲስ ግኝት ጉዞ ነው፡፡ሌሎችን ሰዎች መከተልና መቅዳት ኢየሱስ ክርስቶስ ዋና የስልጠና ዘዴ አድርጎ የመረጣቸው ጥንታዊ የመማሪያ ጥበቦች ናቸው፡፡ከዚህ በጊዜ ከተፈተነ የስልጠና ዘዴ አፍሮ ከመሸሽ ይልቅ የመከተልን ጥበብ ውበትና ያለበትን ጭምትነት ለመረዳት ጊዜው አሁን ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ማንን፣ ምንን እና እንዴት በሚገባ መከተል እንደሚገባህ ትማራለህ፡፡ይህ የዳግ ሂዋርድ ሚልስ ድንቅ መጽሐፍ ለመከተል ጥበብ በክርስትና ልምምዳችን ውስጥ ተገቢውን ቦታ ይሰጠዋል፡፡

  • ጥበብን ማዳበር ችሎታን ወይንም ክህሎትን ማዳበር ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር ሞገስ አዋቂ ለሆኑት ትመጣለች ይላል። የአገልግሎትም ሥራ ትልቅ ችሎታን ይጠይቃል። ይህ « የአገልግሎት ጥበብ » በመባል የወጣው አዲስ መጽሐፍ የአገልግሎትን ሥራ መስራት ለሚፈልጉ በጣም አስፈላጊ ነው። ስለ አገልግሎት ትክክለኛና ትክክል ያልሆነ አስተሳሰብ ምን እንደሆነ፣የአገልግሎት ሥራ ምንድን ነው፣ በአገልግሎቱ ሥራ ውስጥ ካንተ የሚጠበቀው ምንድን ነው እና የአገልጋይነቴን ተግባር እንዴት ነው የምወጣው የሚሉትን በማብራራት በግልጽ ያስቀምጠዋል። በአገልግሎት ውስጥ ያንተን ተግባር እንዴት መሥራት እንዳለብህ ያሳስብሃልን? ይህ ልዩ የሆነ የዳግ ሂዋ

  • በእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ ውስጥ ከመሆን ይበልጥ ጠቃሚ የሆነ ርዕስ የለም፡፡ የወንጌል አገልጋዮችን የሚለያቸው አንድ ነገር ቢኖር የእግዚአብሔርን ድምፅ በትክክል የመስማት ችሎታቸው ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስን ወደ እግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ መከተል እንዴት ጠቃሚ ነገር ነው፡፡ በእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ ውስጥ ስትሆን ታብባለህ ደግሞም ለእግዚአብሔር ማድረግ የምትፈልገውን ሁሉ ከግብ ታደርሳለህ፡፡ ይህ የዳግ ሂዋርድ ሚልስ ድንቅ መፅሐፍ በሕይወትህና በአገልግሎት ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ያደርጋል፡፡

  • ላይኮስ የሚለው የግሪክ ትርጉሙ ክህሎት የሌለው ማለት ነው፡፡ታሪክ በተደጋጋሚ 'ልዩ ክህሎት' ባልተጎናጸፉ ሰዎች ታላላቅ ሁነቶች እንደተከወኑ ያስተምረናል በትርፍ ጊዜያቸው የሚገለግሊ ሰዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ የማይሰሩ ከሆነ፣ ሸክምን በትርፍ ጊዜያቸው ለሚያገለግሉ ሰዎች ማካፈል እና ለምን የትርፍ ጊዜ አገልግሎትን ለመጠበቅ መዋጋት እንዳለብን በዚህ የዳግ ሂዋርድ ሚልስ ዓይነተኛ መጽሐፍ አማካኝነት ተማር፡፡

  • ለአገልግሎት መጠራት ለመሪነት መጠራት ነው፡፡ በድጋሚ፣ በቀላሉ በቀረበና ሊተገበር በሚችል አቀራረብ ዶክተር ሂዋርድ ሚልስ ልዩ ክርስቲያን መሪ ያደረጉትን መርሆች ያብራራል፡፡ በዚህ የተገለጠው እውነት ብዙዎችን ለመሪነት ጥበብ ያነሳሳል፡፡

  • በምድር ላይ የሰው ሕይወት ሰልፍ እንደሆ ታውቃለህን¬? በጦርነት ውስጥ መሆን ብትፈልግም ባትፈልግም ያለንው በጦርነት ውስጥ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር የሰው ሕይወት ብርቱ ሰልፍ ነው ይላል። መልካሙን ገድል እየታገልክ ጦርነቱን ማሸነፍ አለብህ። ይህ ስለውጊያ የሚያስተምረው አዲስ መጽሐፍ መሪዎች በሙሉ ሊያነቡት የሚገባ ነው።

  • ኢየሱስ ሲናገር፡- እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ። በእውነትም እባቦች ልባሞች ናቸውን? ኢየሱስ ለምንድን እንደዚህ ያለ ምክር ሰጠ? ግልጥ አድርጎ የሚያስረዳውን የዳግ ሂዋርድ ሚልስን መጽሐፍ ያዝና ድብቅ የሆኑትን የእባብ ብልሀቶች ተማ

  • ይህ የሚያስደንቅ መጽሐፍ እየሰራ ያለውን መርገም እንድንቋቋም እና ታላቅነትህን እየተዋጋህ ያለውን መርገም ጸጥ ማሰኘት እንድትችል ይረዳሃል። ማንም ብትሆን እግዚአብሔር ላንተ ትልቅ የህይወት ፍጻሜ አለው። የእርግማንን ሃይል ለምቋቋም ይህን መጽሐፍ እንደ ትልቅ መሳሪያ ተጠቀምበት።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ስለተለያዩ የደም ዓይነቶች ይናገራል፤ የፍየሎች ደም፣የበጎች ደም፣የእርግቦች ደም! እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር ካለ ደም ሥርየት የለም ይላል። በመሆኑም እነዚህ የተለያዩ የደም ዓይነቶች ኃጢያታችንን ያስወግዱልናልን? መልሱ ግልጽ የሆነ አይደለም ነው። ታዲያ ኃጢያታችን ሊያስወግድልን የሚችል ምንድ ነው? ከኢየሱስ ክርስቶስ ደም ሌላ ምንም የለም! ኃጢያታችን ሊያስወግድ እና ድነትን ሊሰጠን የሚችለው የኢየሱስ ደም ብቻ ነው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ስለኢየሱስ ክርስቶስ ደም ብዙ የተቀደሱ እውነታዎችን ታገኛለህ። የኢየሱስ ደም እንዴት ህይወት እንደሚሰጥና እንዴት ትልቅ ዋጋ ያለው እንደሆነም ትደርስበታለህ። እንዲሁም በመን

Title

Go to Top