-
डाग हेवार्द-मिल्स अनेक पुस्तकांचे लेखक आहेत, त्यात उत्कृष्ठ म्हणजे ‘’प्रामाणीकपणा आणि अप्रामाणीकपणा.’’ दोन हजार मंडळयांचा पंथ ज्याला द लाईटहाउस चापेल आंतरराष्ट्रीय असे म्हंटले जाते त्याचे ते संस्थापक आहेत. डाग हेवार्द-मिल्स, एक आंतरराष्ट्रीय सुवार्तिक, हे आंतरराष्ट्रीय येशूच्या आरोग्याच्या सभा आणि परिषदा ह्यात सेवा करतात. अधिक माहितीसाठी, www.daghewardmills.org ह्या संकेतस्थळाला भेट द्या.
-
በድሮ ጊዜ የነበሩት ነቢያቶች ለኛ የትገለጠውን ታላቁን ድነት አጥብቀው ይፈልጉት እንደነበር ታውቃለህ?ይህ ድነት ለሰው ልጆች እንዴት እንደሚደርስ መገመት አይችሉም ነበር…እኛ ግን ይህን ድነት ለመቀበል ታድለናል። ድነትን የተቀበልነው አንድ ሰው ስለነገረን ንው። በዚህ ድንቅ መጽሐፍ ወንጌላዊው ዳግ ሂዋርድሚልስ ታላቁን መዳናቸንን እንድንረዳ ብቻ ሳይሆን፤ እንዴትም አድርግን ይህንን ታላቅ የድነት ወንጌል ለሌሎች ማካፈል እንደምንችል ያሳዩናል። ሁላችንም የወንጌላዊን ስራ የምንሰራ እንሁን!
-
ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ፥ በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት። እናንተ ግን ይቅር ባትሉ በሰማያት ያለው አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም። (ማር.11:25-26) እነዚህን ሁለት ጥቅሶች ማድረግ ያንቀጠቅጥሃል? ከሆነ መፍተሄው እዚህ አለልህ። በዚህ በጣም አስፈላጊ በሆነው መጽሐፍ ውስጥ በቀላሉ ይቅር ማለትን ትማራለህ፤ እንደዚሁም የሰማዩ አባትህን ይቅርታ ትጠግባለህ። በቀላሉ እና ከልብህ ይቅር ማለት እስክትችል ድረስ ይህ መጽሐፍ አብሮህ ይኑር።
-
ዳግ ሂዋርድ ሚልስ፣ በርካታ ተፈላጊ መጽሐፍ የጻፉና ከእነዚሁም ውስጥ “ታማኝነትና ታማኝ አለመሆን” የተባለው በዓለም ላይ ታዋቂ በሆነውን መጽሐፋቸው ይታወቃሉ። በአሁኑ ጊዜ ዩናይትድ ዲኖምኔሽን ኦርጂኔትድ ፍሮም ዘ ላይትሃውስ ግሩፕ ኦፍ ቸርች (United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches) ተብሎ የሚጠራው ቤተ ክርስቲያን መስራች ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሶስት ሺህ ቤተክርስቲያኖች አሉት። ዳግ ሂዋርድ ሚልስ፣ በዓለማቀፍ ደረጃ ወንጌላዊ ሲሆኑ “ፈዋሹ ኢየሱስ ክሩሴድ (HEALING JESUS CRUSADE) ” በተሰኘው እና በአለም ዙሪያ በተለያዩ ኮንፈረንሶች ላይ በአገልግሎታቸው ይታወቃሉ፡፡ ይበልጥ መረጃ ከፈለጉ ድህረ ገጻቸውን ይጎብኙ፣ www.daghewardmills.org.
-
መጽሐፍ ቅዱስ ስለተለያዩ የደም ዓይነቶች ይናገራል፤ የፍየሎች ደም፣የበጎች ደም፣የእርግቦች ደም! እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር ካለ ደም ሥርየት የለም ይላል። በመሆኑም እነዚህ የተለያዩ የደም ዓይነቶች ኃጢያታችንን ያስወግዱልናልን? መልሱ ግልጽ የሆነ አይደለም ነው። ታዲያ ኃጢያታችን ሊያስወግድልን የሚችል ምንድ ነው? ከኢየሱስ ክርስቶስ ደም ሌላ ምንም የለም! ኃጢያታችን ሊያስወግድ እና ድነትን ሊሰጠን የሚችለው የኢየሱስ ደም ብቻ ነው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ስለኢየሱስ ክርስቶስ ደም ብዙ የተቀደሱ እውነታዎችን ታገኛለህ። የኢየሱስ ደም እንዴት ህይወት እንደሚሰጥና እንዴት ትልቅ ዋጋ ያለው እንደሆነም ትደርስበታለህ። እንዲሁም በመን