-
ጥበብን ማዳበር ችሎታን ወይንም ክህሎትን ማዳበር ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር ሞገስ አዋቂ ለሆኑት ትመጣለች ይላል። የአገልግሎትም ሥራ ትልቅ ችሎታን ይጠይቃል። ይህ « የአገልግሎት ጥበብ » በመባል የወጣው አዲስ መጽሐፍ የአገልግሎትን ሥራ መስራት ለሚፈልጉ በጣም አስፈላጊ ነው። ስለ አገልግሎት ትክክለኛና ትክክል ያልሆነ አስተሳሰብ ምን እንደሆነ፣የአገልግሎት ሥራ ምንድን ነው፣ በአገልግሎቱ ሥራ ውስጥ ካንተ የሚጠበቀው ምንድን ነው እና የአገልጋይነቴን ተግባር እንዴት ነው የምወጣው የሚሉትን በማብራራት በግልጽ ያስቀምጠዋል። በአገልግሎት ውስጥ ያንተን ተግባር እንዴት መሥራት እንዳለብህ ያሳስብሃልን? ይህ ልዩ የሆነ የዳግ ሂዋ
-
በዚህ ለየት ባለ መጽሐፍ ውስጥ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ ስለ ትዳር ሰፋ ያለ ተጨባጭ ነገሮችን ያሳዩናል። ይህ ልዩ ምጽሐፍ ለአስተማሪውም ሆነ ለትዳር ጥንዶቸ ዝግጁ መገልገያ ነው። ትዳራችሁን የሚያሳምሩ እና የሚያስደስቱ ጠቋሚ ነገሮችን በእርግጥ ያገኙበታል። ይህ መጽሐፍ ከጋብቻ በፊት በትዳር ውስጥ እና ከትዳር በኋላ ላሉት ለሰው ልጆች ህብረት ውድ የሆኑ መሰረታዊ እና ተግባራዊ መረጃዎችን ያዘለ ነው። ስለ ወሲብ፤ ስለ ውልደት፤ ስል እርግዝና እና ልጅ ከመጣ በኋላ በሰው አካል አስተምሮ ላይ ተመርኩዞ በትልቅ ጥናት ተደርጎበት የተዘጋጀ ነው። የመጽሐፉ ዋነኛነት ውስብስብ ያለን መረጃ ቀላል እና ለመረዳት በሚያስችል መንገድ የዶክተር ዳግ ሂዋርድ ሚልስ አቀማመጥ ነው። በአጠቃላይ ሰለ ትዳር ገለጻ ፤ በጣም የጠለቅ፣ ለአጠቃቀም ቀላል በሆነ መንገድ የቀረበ መጽሐፍ ነው። ሰለ ጋብቻ ምክር የቢሾፕ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ መጽሐፍ አቻ የልውም። የህክምና ዶክተር መሆኑ በግልጽ ያሳያችውና ያንጽባረቃችው፣ በተለይ በግል የህክምና አይኖቹ አገላልጽ የዚህን መጽሐፍ ልዩ መሆኑን ያንጽባርቃል። ኤድዊን ሞርጋን ኦጎ፣ የጋና የህክምና ዩኒቨርስቲ አስተማሪ
-
በህይወት ጉዞ ውስጥ ስትጓዝ የማይታየው አለም የእውነተኛው እንደሆነና ተፈጥሮዋዊው ደግሞ የማይታየው አለም መገለጥ እንደሆነ ግልጥ እያለ ይታወቅሃል። ግልጥ ያሉ ጠላቶች እንዳሉህ ሁሉ ድብቅ ጠላቶችም አሉህ። ጠላትህን ሳታውቀው፤ ስልቱን ሳትረዳ፤ አሰራሩን እና መሳሪያውን ሳታውቅ ልትዋጋው ትችላለህን? ለህይወትህ ጉዞ ይህ መጽሐፍ ዋነኛ ነው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የማይታየው ጠላትህ ማን እንደሆነ፤ የህልውናቸው ስር መሰረት፤ ባህሪያቸው እና እንዴት እንደምታሸንፋቸው ትማራለህ።ይህ ውድ መጽሐፍ የማይታዩትን ጠላቶችህን እንድትቋቋማቸው ይርዳህ!
-
እግዚአብሔርን መከተል አስደሳች የአዳዲስ ግኝት ጉዞ ነው፡፡ሌሎችን ሰዎች መከተልና መቅዳት ኢየሱስ ክርስቶስ ዋና የስልጠና ዘዴ አድርጎ የመረጣቸው ጥንታዊ የመማሪያ ጥበቦች ናቸው፡፡ከዚህ በጊዜ ከተፈተነ የስልጠና ዘዴ አፍሮ ከመሸሽ ይልቅ የመከተልን ጥበብ ውበትና ያለበትን ጭምትነት ለመረዳት ጊዜው አሁን ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ማንን፣ ምንን እና እንዴት በሚገባ መከተል እንደሚገባህ ትማራለህ፡፡ይህ የዳግ ሂዋርድ ሚልስ ድንቅ መጽሐፍ ለመከተል ጥበብ በክርስትና ልምምዳችን ውስጥ ተገቢውን ቦታ ይሰጠዋል፡፡