-
በእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ ውስጥ ከመሆን ይበልጥ ጠቃሚ የሆነ ርዕስ የለም፡፡ የወንጌል አገልጋዮችን የሚለያቸው አንድ ነገር ቢኖር የእግዚአብሔርን ድምፅ በትክክል የመስማት ችሎታቸው ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስን ወደ እግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ መከተል እንዴት ጠቃሚ ነገር ነው፡፡ በእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ ውስጥ ስትሆን ታብባለህ ደግሞም ለእግዚአብሔር ማድረግ የምትፈልገውን ሁሉ ከግብ ታደርሳለህ፡፡ ይህ የዳግ ሂዋርድ ሚልስ ድንቅ መፅሐፍ በሕይወትህና በአገልግሎት ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ያደርጋል፡፡
-
አመጸኛ ሰዎች የተደረገላቸውን ነገር አያስታውሱም፣ ብዙ ጊዜም የተወሰኑ ነገሮችን ለመዘንጋት ይመርጣሉ፡፡ ጌታ ለይሁዳ ያደረገለትን ነገር አላስታወሰም፣ ከኢየሱስ ያያቸውንና የሰማቸውንም ነገሮች አላስታወሳቸውም፡፡ አሁን ‘ይሁዳ’ ብለን የምናውቀውን አጸያፊ ባህሪ ያወቅነው ለዚህ ነው፡፡ የማስታወስ ችሎታ አንድ አገልጋይ ሊኖሩት ከሚገቡት እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ መንፈሳዊ ባሕርያት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ የማያስታውሱ ሰዎች፣ ስኬታማ የመሆናቸው እድል እጅግ የጠበበ ነው፡፡ በቀላሉ ወደ ተወሰኑ ከፍታዎች መድረስ ያቅታቸዋል። ይሄ የተለየ እና እምብዛም የማይታወቀው የዚህ መጽሐፍ ርዕሥ፣ ከእግዚአብሔር ለአንተ የተሰጠ ስጦታ ነው
-
ብዙዎቻችን መልካሙን እና ክፉውን ስለያዘው ዛፍ ብዙ አናውቅም። የምናስበው ለአዳም እና ለሔዋን የደረሰባቸው መጥፎ ነገር ሆኖ እኛ ያመለጥነው ይመስለናል። መልካሙን እና ክፉውን ከያዘው ዛፍ ያመልጥክ ይመስልሃል? በዚህ ቀጥትኛ በሆን መጽሐፍ ወስጥ መልካሙን እና ክፉውን ያዘው ዛፍ እየሰራ እንደሆን ታውቃለህ። አዳምን እና ሔዋንን የፈተናችው ዛሬም ለእኛ እንደዚያው እያቀረበልን እንደሆነ ታውቃለህ። እንደዚሁም በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያልውን እውቅት በመጠቀም በህይወትህና በአገልግሎትህ ውስጥ የሚያልፈውን ነገር እንድታይ ይረዳሃል።
-
እግዚአብሔርን ማገልገል ትልቅ ነገር እንደሆን ሰምተህ ልታውቅ ትችላለህ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ማገልገል እንዴት ትልቅ ነገር እንደሆነ ጠለቅ ብልህ አስበህ ላታውቅ ትችላለህ። በዚህ ለየት ባልው የዳግ ሂዋርድ ሚልስ መጽሕፍ ውስጥ ማን የእግዚአብሔር አግልጋይ እንደሆነ እና እንዴት እግዚአብሔርን ማገልገል እንዳለብህ ትረዳለህ። እግዚአብሔርን ብሚያገለግሉት እና እግዚአብሔርን በማያገልግሉት መካክል ያልው ልዩነት ግልጽ ባለው መንገድ ይብራልህ! እግዚአብሔርን ክሚያገለግሉት ውስጥ የምትቆጠር ሁን!