ዳግሂዋርድሚልስ፣በርካታተፈላጊመጽሐፍየጻፉናከእነዚሁምውስጥ“ታማኝነትናታማኝአለመሆን” የተባለውበዓለምላይታዋቂበሆነውንመጽሐፋቸውይታወቃሉ።በአሁኑጊዜዩናይትድዲኖምኔሽንኦርጂኔትድፍሮምዘላይትሃውስግሩፕኦፍቸርች(United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches) ተብሎየሚጠራውቤተክርስቲያንመስራችናቸው፡፡በአሁኑጊዜሶስትሺህቤተክርስቲያኖችአሉት።
ዳግሂዋርድሚልስ፣በዓለማቀፍደረጃወንጌላዊሲሆኑ“ፈዋሹኢየሱስክሩሴድ(HEALING JESUS CRUSADE) ” በተሰኘውእናበአለምዙሪያበተለያዩኮንፈረንሶችላይበአገልግሎታቸውይታወቃሉ፡፡ይበልጥመረጃከፈለጉድህረገጻቸውንይጎብኙ፣www.daghewardmills.org.

  • ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ለምን አንድን ሰው ይፈልጋል? ጌታ ከእርስዎ ምን ይፈልጋል? እግዚአብሔር ለራሱ ማድረግ የማይችለው ምንድን ነው? እግዚአብሔር ብቻውን ማከናወን የማይችለው ምንድን ነው? እግዚአብሔር በእርሱና በሰው መካከል የሚቆም ሰውን ይፈልጋል። እግዚአብሔር ለታናናሾቹ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥ ሰውን ይፈልጋል! እግዚአብሔር ከደኅንነት የራቁትን ልጆች የሚያድን ሰውን ይፈልጋል! መጽሐፍ ቅዱስ “እግዚአብሔር ሰውን ፈለገ...” ይላል! በዚህ ልብን በሚያሞቅ መጽሐፍ አማካኝነት በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ፈቃደኛ ዕቃ የመሆን ፍላጎትዎ ይነሳሳል! ከእንግዲህ ተራ አባል በመሆን ብቻ አይረኩም። ረዳት ይሆናሉ! ልክ እንደ ታዋቂው የዝማሬ ደራሲ “ጌታ ሆይ፣ አንድ ሰው እንደሚያስፈልግህ አውቃለሁ! በእኔ ላይ መታመን ትችላለህ!” ይላሉ።  
  • መጽሐፍ ቅዱስ በሺዎች በሚቆጠሩ ነፍሳት የተሞላች የሐዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያንን ይገልጥልናል። አንዲት ቤተክርስቲያን በሺዎች የሚቆጠሩ ነፍሳት ሲኖሯት፣ እሷ ሜጋ ቸርች (ታላቅ ቤተክርስቲያን) ናት። እግዚአብሔር በልብዎ ውስጥ ሜጋ ቸርች የመገንባት ራዕይ ካስቀመጠ፣ ያንን ህልም እውን ለማድረግ የሚረዳዎት መጽሐፍ ይህ ነው። ደራሲው ዳግ ሂዋርድ-ሚልስ (Dag Heward-Mills)፣ በዚህ አስደናቂ መጽሐፍ ውስጥ ዲያብሎስ ለምን ጉባኤን እንደሚቃወም ያብራራሉ፤ እንዲሁም 1000 ትናንሽ እንደ ዘር ያሉ "ማይክሮ" አብያተ ክርስቲያናትን የመትከል ቀላል እርምጃዎች እንዴት ሜጋ ቸርች ለመገንባት እንደሚረዱዎት ይዘረዝራሉ። በ1000 ማይክሮ አብያተ ክርስቲያናት ኃይለኛ ተፅዕኖ አማካኝነት አገልግሎትዎ ይለወጥ!
  • መጽሐፍ ቅዱስ እንድንጸልይ በሚያበረታቱ ምክሮች የተሞላ ነው፦ "ሁሉንም ነገር በጸሎት! ሁልጊዜ መጸለይ! ሰው ዘወትር ሊጸልይ ይገባዋል! ሁልጊዜ ጸልዩ! ሳታቋርጡ ጸልዩ!" "ሁሉ ነገር በጸሎት፣ ያለ ጸሎት ምንም ነገር የለም" ("Everything by prayer, nothing without prayer") በተሰኘው በዚህ ድንቅ መጽሐፍ ውስጥ፣ የኢየሱስ ክርስቶስን የጸሎት ሕይወት መንገዶችና አርአያነት የሚያስተምር ጉዞ ትጀምራላችሁ። ኢየሱስ ከጸለየ፣ እናንተና እኔ ይልቁኑ ልንጸልይ ይገባል። በሕይወታችን ውስጥ ያለው ነገር ሁሉ በጸሎት ሊሳካ ይችላል፤ ያለ ጸሎት ግን ምንም ሊሳካ አይችልም። ይህንን ሳቢ መጽሐፍ ካነበቡ በኋላ የጸሎት ሕይወትዎ አስደሳች ይሆናል!
  • እግዚአብሔር ሕይወትን እስከሰጠን ድረስ፣ ታላቅ ነገር የማድረግ ዕድል አለን። ዛሬ ለእግዚአብሔር ታላላቅ ነገሮችን ለመሞከር ዕድል (ለውጥ) አለዎት። ቢያንስ ይሞክሩ! ጥረት ያድርጉ! ይህ መጽሐፍ እግዚአብሔር እንድትሆኑ የፈጠራችሁን ምርጥ ማንነት እንድትሆኑ ያበረታታችኋል። በየቀኑ ለእግዚአብሔር ታላላቅ ነገሮችን ለማድረግ ይወስኑ፤ በእግዚአብሔርም ጸጋ ማድረግ በሚችሉት ነገር ይደነቃሉ። የመጽሐፉን ይዘት በትጋት ሲያጠኑና ለእግዚአብሔር ታላቅ ነገር ለማድረግ ሲሞክሩ ታላላቅ ስኬቶች ይጠብቁዎታል! ለእግዚአብሔር ታላቅ ሥራን (exploits) ያድርጉ!
  • ኢየሱስ ክርስቶስ ብልጽግናንና ሀብትን የሚገዛውን አስደንጋጭ መርህ ገልጦልናል፡፡ ያለው ይበልጥ ይኖረዋል! እንዴት አግባብ ያልሆነ ነገር ይመስላል! ሆኖም ግን በየእለቱ በፊታችን የሚሆነው ነገር ይህ እውነታ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ ጥቂት የተረዳነውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ለማብራራት ይሞክራል፡፡ ይህንን የዳግ ሂዋርድ ሚልስ አዲስ መጽሐፍ ስታጠና ስለ ብልጽግናም ምሥጢራት ታላላቅ እይታዎችን ትቀበላለህ፡፡

  • ላይኮስ የሚለው የግሪክ ትርጉሙ ክህሎት የሌለው ማለት ነው፡፡ታሪክ በተደጋጋሚ 'ልዩ ክህሎት' ባልተጎናጸፉ ሰዎች ታላላቅ ሁነቶች እንደተከወኑ ያስተምረናል በትርፍ ጊዜያቸው የሚገለግሊ ሰዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ የማይሰሩ ከሆነ፣ ሸክምን በትርፍ ጊዜያቸው ለሚያገለግሉ ሰዎች ማካፈል እና ለምን የትርፍ ጊዜ አገልግሎትን ለመጠበቅ መዋጋት እንዳለብን በዚህ የዳግ ሂዋርድ ሚልስ ዓይነተኛ መጽሐፍ አማካኝነት ተማር፡፡

  • መጽሐፍ ቅዱስ በፊሊጵስዮስ ፪፡፬ ላይ “እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ።” ይላል። በዚህ ይጊዜው መጽሐፍ ውስጥ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ ከራስህ ማሰብ አልፈህ ስለሌሎች ማስብ እንድትጀምር ያበረታታሃል። ሌሎችንም ደግሞ ወደድ!ደግሞም ሌሎችን አስብ! ለሌሎቸም ደግሞ ተጠንቀቅላቸው!ደግሞም ለሌሎቸ መኖር ጀምር! ኢየሱስ መጥቶ የሞተበት ምክንያት ለሌሎች በማሰብ ነው። እኔ እንደ እርሱ መሆን እፈልጋለሁ። እንደ ኢየሱስ መሆን ትፈልጋለህ?

  • ኢየሱስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በአምስት የተለያዩ አጋጣሚዎች ላይ «ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት» የሚለውን ሐረግ ተጠቅሟል። ይህ ዝግጁ ሳይሆኑ ወደ መንግሥተ ሰማያት በመግባት ምክንያት የሚመጣውን ሕመም፣ ቁጣ፣ ሐዘን፣ ጸጸት፣ ፀፀት እና የኪሳራ ስሜት የሚያመለክት ትንቢታዊ ማስጠንቀቂያ ነው። ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ውስጥ የሚወድቁት ሁሉ በሰማይ ሊያገኙት ይችሉ የነበረውን የዘላለም ሽልማት ያጡ ናቸው! ሊኖራቸው ይችል የነበረውን ደስታ ያጣሉ፣ እንዲሁም የክብርን አክሊሎች ያጣሉ። ታዋቂው ደራሲ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ (Dag Heward-Mills)፣ በለመደው ግልጽ በሆነ የአጻጻፍ ስልቱ፣ ብዙዎች በምድር ላይ ሳሉ ስላመለጧቸው ዕድሎች የሚሰማቸውን አስፈሪ የጸጸት እውነታ ይገልጻል። በጸጸት ውስጥ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ከሚሆንባቸው ሰዎች መካከል አንዱ እንዳትሆን የሚቻለህን ሁሉ ማድረግ ይኖርብሃል!
  • ይህ መጽሐፍ የሴት ልጆችን ጉዳት ይፈውሳል! በእዚህ ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረ መጽሐፍ፣ ሴቶች የሚገጥሟቸውን በርካታ አዳጋች ሁኔታዎችን በእግዚአብሔር ጥበብ እርዳታ እንዲያሸንፉ ይነሳሳሉ፡፡ ይህን በተለይ ለሴት ልጆች የተጻፈ ኃይለኛና አዲስ መጽሐፍ ስታነብቢ እግዚአብሔር ሕይወትሽን በመንካት ያበረታሻል፡፡

  • በምድር ላይ የሰው ሕይወት ሰልፍ እንደሆ ታውቃለህን¬? በጦርነት ውስጥ መሆን ብትፈልግም ባትፈልግም ያለንው በጦርነት ውስጥ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር የሰው ሕይወት ብርቱ ሰልፍ ነው ይላል። መልካሙን ገድል እየታገልክ ጦርነቱን ማሸነፍ አለብህ። ይህ ስለውጊያ የሚያስተምረው አዲስ መጽሐፍ መሪዎች በሙሉ ሊያነቡት የሚገባ ነው።

  • መጽሐፍ ቅዱስ “ታማኝ ሰውን ማን ያገኘዋል?” የሚለውን ወሳኝ ጥያቄ ይጠይቃል። ይህ የሚያሳየው ታማኝነት (Loyalty) የሚባለውን ውድ ባሕርይ በአንድ ሰው ላይ ማግኘት ምን ያህል ብርቅ እንደሆነ ነው። አንዳንዶች የክርስትና ጉዟቸውን በቅንዓትና በፍላጎት ጀምረው ለምን በመንገድ ላይ እንደሚዝሉ ጠይቀው ያውቃሉ? በመጀመሪያ የታየው ያ ሁሉ ግለት ለምን አንዳንድ ጊዜ ወደ ውድመት ይለወጣል? ሊከሰት ላለው መንፈሳዊ ጥፋት (የመርከብ መሰባበር) ማስጠንቀቂያ ሊሆኑ የሚችሉ የቅድመ-ምልክቶች አሉ? በዚህ ማራኪ መጽሐፍ ውስጥ፣ ዳግ ሂዋርድ-ሚልስ (Dag Heward-Mills) በእውነተኛው የባሕር ላይ መርከብ መሰባበር እና በብዙ አገልግሎቶች ላይ በሚደርሱ መንፈሳዊ ጥፋቶች መካከል ያለውን አስገራሚ ተመሳሳይነት ያሳያሉ። የቅድመ-ማስጠንቀቂያ ምልክቶቹን ይወቁ፣ ወጥመዶቹን ያስወግዱ፣ እንዲሁም የሚገጥምዎት ማዕበል ምንም ይሁን ምን በእምነትና በጽኑ አቋም ጸንተው እንዴት መቆም እንደሚችሉ ይማሩ።
  • ይህ የሚያስደንቅ መጽሐፍ እየሰራ ያለውን መርገም እንድንቋቋም እና ታላቅነትህን እየተዋጋህ ያለውን መርገም ጸጥ ማሰኘት እንድትችል ይረዳሃል። ማንም ብትሆን እግዚአብሔር ላንተ ትልቅ የህይወት ፍጻሜ አለው። የእርግማንን ሃይል ለምቋቋም ይህን መጽሐፍ እንደ ትልቅ መሳሪያ ተጠቀምበት።

Title

Go to Top