ዳግሂዋርድሚልስ፣በርካታተፈላጊመጽሐፍየጻፉናከእነዚሁምውስጥ“ታማኝነትናታማኝአለመሆን” የተባለውበዓለምላይታዋቂበሆነውንመጽሐፋቸውይታወቃሉ።በአሁኑጊዜዩናይትድዲኖምኔሽንኦርጂኔትድፍሮምዘላይትሃውስግሩፕኦፍቸርች(United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches) ተብሎየሚጠራውቤተክርስቲያንመስራችናቸው፡፡በአሁኑጊዜሶስትሺህቤተክርስቲያኖችአሉት።
ዳግሂዋርድሚልስ፣በዓለማቀፍደረጃወንጌላዊሲሆኑ“ፈዋሹኢየሱስክሩሴድ(HEALING JESUS CRUSADE) ” በተሰኘውእናበአለምዙሪያበተለያዩኮንፈረንሶችላይበአገልግሎታቸውይታወቃሉ፡፡ይበልጥመረጃከፈለጉድህረገጻቸውንይጎብኙ፣www.daghewardmills.org.

  • የእግዚአብሔር የዘላለም ዓላማ ለእኛ ፍሬያማ እንድንሆን ነው። በዮሐንስ 15:16 ላይ ጌታ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን “ሄዳችሁ ፍሬ እንድታፈሩ” በማለት መክሯቸዋል። እግዚአብሔር እርስዎን ፍሬ ማፍራት እንዳለበት ዛፍ አድርጎ ይመለከትዎታል። በዚህ ተግባራዊ መጽሐፍ ውስጥ፣ ቢሾፕ ዳግ ሂዋርድ-ሚልስ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወሰዱ የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ የፍሬያማነት ሕጎችን ያሳዩናል። ብዙ ፍሬ — የሚኖር ፍሬ — ለማፍራት ይነሳሳሉ!
  • ይህን እጅግ አስፈላጊ ጥያቄ ቆም ብለህ ጠይቀህ ታውቃለህ? ጸሎት ነገሮችን ይለውጣል! በጸሎት ጊዜህን ስታሳልፍ፣ ቅባት ታገኛለህ እና በመንፈሳዊ ኃይል መንቀሳቀስ ትጀምራለህ። በጸለይህ ቁጥር ሁሉ ከተፈጥሮ በላይ የሆኑ ነገሮች ይከሰታሉ። ማንኛውም የሚያሳስብህ ነገር በጸሎት ሊፈታ ይችላል። ምንም ታላቅ ሰው ባታውቅ ልትጸልይ ትችላለህ! ገንዘብ ባይኖርህም ልትጸልይ ትችላለህ! ቀውስ እስኪመጣ ድረስ አትጠብቅ። አሁኑኑ መጸለይን ተማር!
  • በመጀመሪያ ቃል ነበረ! ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ! ቃልም እግዚአብሔር ነበረ! እግዚአብሔር እና ቃሉ ሁልጊዜም ለማንኛውም ጠቃሚ ነገር መጀመሪያና ማእከል ናቸው። ሕይወትዎ ትርጉም ያለው እንዲሆን ከተፈለገ፣ እግዚአብሔር እና ቃሉ ዋነኛው ነገር መሆን አለባቸው። ጥበብዎ የሚያሳየው የአስተሳሰብ መንገድዎን ነው። ጥበብ ተግባራዊ ሰው ያደርግዎታል። ጥበበኛ ሰው አንድን ነገር ይገነባል። የገነቡት ነገር የእርስዎን ጥበብ ይገልጣል። ጥበብ ለአገልግሎት ለሚያስፈልጉዎት የአመራር ክህሎቶች ዋናው ቁልፍ ነው። ጥበብ የአመራር ፈተናዎችን ለመወጣት ቁልፍ መሳሪያ ነው። ሰለሞን ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብን ለመነ። እግዚአብሔርም ጥበበኛና አስተዋይ ልብን ሰጠው። የዚህ ጥበበኛና አስተዋይ ልብ ውጤት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁሉ ይታያል። ይህ መጽሐፍ ስለ ሰው ብልህነት ወይም ስለ አሳሳች ንግግሮች አይናገርም። ይህ መጽሐፍ ሰዎችን ለማደናገር ስለሚጠቀሙባቸው ከበድ ያሉ ቃላትም አይናገርም። ደራሲው ቢሾፕ ዳግ ሂዋርድ-ሚልስ (Bishop Dag Heward-Mills)፣ የተለያዩ የጥበብ ዓይነቶች ቢኖሩም፣ የእግዚአብሔር ቃል ግን ዋነኛው ነገር መሆኑን ለአንባቢው ለማብራራት ይጥራሉ።
  • እንደ ክርስቲያን በሕይወትህ ካሉ ተጽዕኖዎች ሁሉ እጅግ ታላቁና ጣፋጩ መንፈስ ቅዱስ መሆን አለበት፡፡ ይህ መጽሐፍ ባህርይህ፣ ዕውቀትህ፣ የፈጠራ ችሎታህና የመቀደስ ችሎታህ ሳይቀር እንዴት በመንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖ ሊደረግባቸው እንደሚችሉ መረዳት ያስችልሃል፡፡ በዚህ የዳግ ሂዋርድ ሚልስ ዓይነተኛ መጽሐፍ አማካኝነት መንፈስ ቅዱስ እስከ ወዲያኛው በህይወትህ ላይ ተፅዕኖ እንዲኖረው፣ እንዲያነቃቃህ፣ እንዲገፋፋህና እንዲለውጥህ መፍቀድ አለብህ፡፡

  • ጌታን ትወደዋለህ? ይህ በጣም አስፈላጊ ጥያቄ ነው! ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጴጥሮስን “ጴጥሮስ ሆይ፥ ትወደኛለህን?” ብሎ ጠይቆታል። ለእግዚአብሔር ያለህ ፍቅር ለምን መወያየት የሚያስፈልገው ጉዳይ ሆነ? ኢየሱስ ከሁሉ የሚበልጠው ትዕዛዝ “ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፥ በፍጹም ነፍስህ፥ በፍጹም አሳብህም ውደድ” የሚለው እንደሆነ ተናግሯል። አንዳንድ ጊዜ፣ ጌታ ለእግዚአብሔር ያለዎትን ፍቅር ለማረጋገጥ ሲል ብቻ ፈተና የሚሆኑ ሁኔታዎችን ሊያጋጥሙዎት ይችላል። ጌታን የሚወዱ ከሆነ፣ የፍቅር ፈተናዎችን በማለፍ ፍቅርዎን ያረጋግጡ! ይህ በታዋቂው ደራሲ ዳግ ሂዋርድ-ሚልስ (Dag Heward-Mills) የተጻፈ ሌላ አስደናቂ መጽሐፍ ሲሆን፣ “በእውነት ጌታን እወደዋለሁን?” የሚለውን እጅግ አስፈላጊ ጥያቄ እራስዎን እንዲጠይቁና እንዲያስቡ ያደርግዎታል።
  • አዲስ ሰው (ኖቪስ) ለአንድ ነገር አዲስ የሆነ ነው፤ እርሱ ጀማሪ ነው። እግዚአብሔር አዲስ የተሾመ ወይም አዲስ የተፈጠረ አካል አይደለም። ስለ እግዚአብሔር አዲስ የሚያደርገው ምንም ነገር የለም። እርሱ መጀመሪያ ነው! እግዚአብሔር ለዘላለም የነበረ ነው። እርሱ ሁሉን የሚችል ጌታ አምላክ፣ የዘላለም ጌታ ነው። እኛ ግን አዲስ ሰዎች (ኖቪሶች) የመሆን ዕድላችን ሰፊ ነው። በየቀኑ አዳዲስ ግኝቶችን የምናገኝ እኛ ነን። አዲስ ሰው እንደ ትዕቢት ላሉ ለብዙ አደጋዎች የተጋለጠ ነው። አዲስ ሰው ለዓመታት ለተመሠረቱ ሥልጣናት ራሱን ከፍ አድርጎ እንዲያነሳ የሚያደርገው የአዲስ ሰው ኩራት ነው። ሉሲፈር በትዕቢቱ ምክንያት የተፈረደበት አዲስ ሰው ነበረ! እርሱም በ**«በዲያብሎስ ፍርድ»** ውስጥ ወደቀ። የሉሲፈር ትልቁ ስህተት ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጻጸር ስለራሱ ትክክለኛ ግምት ያልነበረው መሆኑ ነው። በእነዚህ ሐሳብ ቀስቃሽ ምዕራፎች ውስጥ፣ ስለ አዲስ ሰው ኩራት የቀረቡትን ትምህርቶች በሙሉ ጥንቃቄ ትወስዱ ዘንድ ይሁን፤ ያለበለዚያ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሱትን ነጥቦች ሁሉ ለራሳችሁ ጥፋትና ፍርድ ትፈጽማላችሁ። ከአዲስ ሰው አደጋዎች ሁሉ ነፃ ውጡ!
  • በድሮ ጊዜ የነበሩት ነቢያቶች ለኛ የትገለጠውን ታላቁን ድነት አጥብቀው ይፈልጉት እንደነበር ታውቃለህ­?ይህ ድነት ለሰው ልጆች እንዴት እንደሚደርስ መገመት አይችሉም ነበር…እኛ ግን ይህን ድነት ለመቀበል ታድለናል። ድነትን የተቀበልነው አንድ ሰው ስለነገረን ንው። በዚህ ድንቅ መጽሐፍ ወንጌላዊው ዳግ ሂዋርድሚልስ ታላቁን መዳናቸንን እንድንረዳ ብቻ ሳይሆን፤ እንዴትም አድርግን ይህንን ታላቅ የድነት ወንጌል ለሌሎች ማካፈል እንደምንችል ያሳዩናል። ሁላችንም የወንጌላዊን ስራ የምንሰራ እንሁን!

  • ይህ መጽሐፍ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የሚገኘውን መዳን እንድትረዳ ትልቅ የሆነን መረጃ የሚሰጥ ነው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የኢየሱስን ፍቅር ፣ እንዴት ዳግመኛ መወለድ እንደሚቻል፣ ወደ ገሃነም መውረድን እንዴት ማስወገድ እንደሚቻልና በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ሰው መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ መረዳት ትችላለህ። ይህንን መጽሐፍ ለማንም ሰው ስጠው ከዚያም በኢየሱስ ክርስቶስ ደም መዳን (መዋጀት) ምን እንደሆነ ይገባዋል።

  • ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ፥ በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት። እናንተ ግን ይቅር ባትሉ በሰማያት ያለው አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም። (ማር.11:25-26) እነዚህን ሁለት ጥቅሶች ማድረግ ያንቀጠቅጥሃል? ከሆነ መፍተሄው እዚህ አለልህ። በዚህ በጣም አስፈላጊ በሆነው መጽሐፍ ውስጥ በቀላሉ ይቅር ማለትን ትማራለህ፤ እንደዚሁም የሰማዩ አባትህን ይቅርታ ትጠግባለህ። በቀላሉ እና ከልብህ ይቅር ማለት እስክትችል ድረስ ይህ መጽሐፍ አብሮህ ይኑር።

  • ብዙ ተስፋ የቆረጡ ፓስተሮች ይህን ጥያቄ ለራሳቸው ጠይቀዋል፡ "ይህች ቤተ ክርስቲያን ለምን አትሠራም?" ከዚህ ጥያቄ ጋር ትተዋወቃለህ፣ አይደል? አዲስ የተሾምክ ፓስተር ልትሆን ትችላለህ፣ ለብሔራት የተላክ ሚስዮናዊ ልትሆን ትችላለህ፣ የተሳካለት ቤተ ክርስቲያን ቅርንጫፍ የምትጀምር ፓስተር ልትሆን ትችላለህ… ዝርዝሩ ይቀጥላል! ይህ ከእኛ ብዙዎቻችን መልስ የሚያስፈልገን ጥያቄ ነው። በተለመደው ተግባራዊ፣ ቀጥተኛ እና ምድራዊ አቀራረቡ፣ በብዙ ሽያጭ የታወቁት ደራሲ ዳግ ሄዋርድ-ሚልስ፣ ለረጅም ጊዜ መልስ ሲፈልግ የቆየውን ጥያቄ ይመልሳሉ። ይህ መጽሐፍ ቤተ ክርስቲያን ለሚመራ ማንኛውም ሰው፤ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለማካፈል እና ሕዝብን ወደ እግዚአብሔር ለመሰብሰብ ፍላጎት ላለው ማንኛውም ሰው የግድ ሊነበብ የሚገባው መጽሐፍ ነው።
  • ክፋት በመላው ዓለም እንደሚገኘው ሁሉ፣ ዕብደትም በምድር ላይ በእኩል ተሰራጭቷል፤ ቤተ ክርስቲያንም ከዚህ የተለየች አይደለችም — የአእምሮ ጤና ችግሮች ዛሬ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በስፋት ይስተዋላሉ! ከዚህ ቀደም ጤናማ የነበሩ ሰዎች ዕብደት ሳይታወቅና ሳይመረመር በመቅረቱ ምክንያት ወደ ፀረ-ማኅበራዊ፣ ምክንያታዊ ያልሆነ እና እጅግ ሞኝነት ወደ ተሞላበት ባሕርይ ሲበታተኑ ማየት አሳዛኝ ነው። በዚህ ድንቅ መጽሐፍ ውስጥ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቁት ደራሲ ዳግ ሄዋርድ-ሚልስ፣ የተለያዩ የአእምሮ ጤና ችግሮችን ዓይነቶች እና ከዛሬዋ ቤተ ክርስቲያን ጋር እንዴት እንደሚዛመዱ ያብራራሉ፤ ማንኛውም ተራ ሰው ሊያደንቀውና ሊረዳው በሚችል ቀላል መንገድ ቀርቧል። በእርግጥም ዕብደትን ለይቶ ማወቅ መቻል ማስተዋል ባለው ሰው ውስጥ ርኅራኄን ያነሳሳል።
  • ለእያንዳዳችን ሀይወት ውጣ ውረድ አልው። በአብዛኛው ጊዜየሚያጋጥሙንን ችግሮች እንድንወጣቸው የሚያስፈልገን ጥበብን በመለማምድ ነው። ጥበብ ችግርን ተቋቁመን ወደ ተአምራታዊ ሀይወት የሚያስገባን የእግዚአብሔር ሚስጥራዊ እርዳታ ነው። እግዚአብሔር ለክብር ጠርቶሃል። ለክብርህና ለውበትህ መንገድ ሆኖ የትዝጋጀው የእግዚአብሔር ሚስጢራዊ አሰራር ድብቅ አሰራሩ ነው። በመጽሐፍ ውስጥ ያለው መገለጥ ለህይወትህ ድል ይስጥህ። ይህ ምጽሐፍ ለከፍታህ እውቀትን ይስጥህ።

Title

Go to Top