• ከክርስቲያን መሪዎች ውስጥ ታዋቂ የሆነው ዶ/ር ዳግ ሂዋርድ ሚልስ ከሚስጢሮቹ አንዱን እንዲህ በማለት ይናገራል « ማንም ሰው ከእግዚአብሔር ጋር የምታደርገው ህብረት ውስጥ ትልቁ ሚስጢር ምንድ ነው ብሎ ቢጠይቀኝ ፣ካለምንም ጥርጥር የምመልስለት በየቀኑ ከእግዚአብሔር ጋር የማደርገው የጥሞና ጊዜ ኃይል ነው እላለሁ »። ይህን መጽሐፍ ለመጻፍ የወሰነው ፣ አንተም የጥሞናን ጊዜን ኃይል ትርፉን እንድታገኝ በማሰብ ነው።

  • በዚህ ጥልቅ እውቀት በሚያስጨብጥ መጽሐፍ፣ ዳግ ሂዋርድ-ሚልስ (Dag Heward-Mills) በቤማ (BEMA) — በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት — ምን እንደሚከሰት ይወያያሉ። ምንም እንኳን ኃጢአታችን ይቅር ቢባልም፣ ሁሉንም አማኞች የሚጠብቅ ፍርድ አለ። ፍርዱም በእርስዎ ተግባራት፣ በተሰወሩ ነገሮች እና ለድርጊቶችዎ በነበሩዎት ውስጣዊ ምክንያቶች (motives) ላይ የተመሰረተ ይሆናል። ውሳኔዎች በሕይወት ውስጥ በጣም አስፈላጊ ናቸው። የፍርድ አለመኖር ማለት የውሳኔዎች አለመኖር ማለት ነው! የፍርድ አለመኖር ወደ ትርምስ ይመራል! ደራሲው እንደ “ፍርድ ምንድን ነው?”፣ “ለምን ፍርድ ያስፈልጋል?” እና እግዚአብሔር ለምን ፍርድን ይወዳል ለሚሉ ጥያቄዎች የሰጡት አስተዋይ ምላሽ፤ ለፍርድ ቀን ዝግጁ ለመሆን ፍርድ እና ፍትህ መጠናት፣ መታወቅ እና መማር ያለባቸው ነገሮች መሆናቸውን ወደ መረዳት ያደርስዎታል።
  • “... በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።” ማቴዎስ 24:14 የምታውቀውን ሕይወት ምን ሊያበቃው ይችላል? በሕይወትህ ውስጥ ያሉት ነገሮች ሁሉ እንዲያበቁ የማድረግ ኃይል ያለው ምንድን ነው? በዚህ ምድር ላይ ያለው የአገልግሎትህ ማብቂያ ምልክት ምን ይሆን? ለቤተ ክርስቲያን መቋጫ የሚሆንባት ምንድን ነው? የሁሉም ነገር መጨረሻ ሞት ነው! በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ካሉት ገጸ-ባህሪያት መካከል ብዙዎቹ አሳዛኝ ለሆነ መጨረሻ በቅተዋል። ሕይወታቸው ለምን እንደተቋጨ ማወቁ አስፈላጊ ነው። የሰዎች አገልግሎት ለምን ወደ ማብቂያው እንደሚመጣ ማወቅ ጠቃሚ ነው። በዚህ ገላጭ መጽሐፍ አማካኝነት ኩራት፣ አለመታዘዝ፣ ጥላቻ፣ ጠማማነት፣ ዓመፅ እና አለማክበር ሕይወትህንና አገልግሎትህን ሊያበቁ ከሚችሉ አሳዛኝ ነገሮች መካከል ጥቂቶቹ መሆናቸውን ትረዳለህ። ከዚህ ጥልቅ ሐሳብ ካለው መጽሐፍ ታላቅ ጥበብን ስትቀበል፣ አገልግሎትህ በዚያው ተመሳሳይ በሆነ አውዳሚ መንገድ ከመጠናቀቅ እንዲድን እመኛለሁ።
  • ቤተ ክርስቲያናትን መትከል ካሪዝማቲክ በሆኑ አገልጋዬች ዘንድ በሰፊው የተለመደ ክስተት ነው፡፡ የቀደምት ደቀ መዛሙርት ዋና እንቅስቃሴ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ስኬታማ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ለማካሄድ በርካታ ጭብጦችን ያካተተ ክህሎትን ይጠይቃል፡፡ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ፣ በመላው ዓለም ከ 1200 በላይ አጥቢያዎች ያሏት ቤተ ክርስቲያን መስራችና መጋቢ ሲሆኑ፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተለያዮ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ግብአቶችን ይተነትናሉ፡፡ ይህ መጽሐፍ ቤተ ክርስቲያን መትከልን የሕይወት ግቡ ማድረግ ለሚፈልግ አገልጋይ የስልጠና ማንዋል ነው።

  • «በበግ ለምድ ከሚመጡ ተኩላዎች ተጠንቀቁ!» — ይህ በዚህ በዘመን መጨረሻ ከመቼውም ጊዜ በላይ በኃይል የሚያስተጋባ የክርስቶስ የዘመን የማይሽረው ማስጠንቀቂያ ነው። በጣም ተፈላጊ በሆኑት ደራሲ ዳግ ሂዋርድ-ሚልስ (Dag Heward-Mills) በተጻፈው በዚህ ማራኪና ድንቅ መጽሐፍ ውስጥ፣ በዛሬዋ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተሸሽገው የሚገኙትን የተኩላዎች ተንኮለኛ ተፈጥሮ ይረዳሉ። በኃይለኛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መገለጦች አማካኝነት፣ ይህ መጽሐፍ የተኩላዎችን ባሕርይ ያጋልጣል እንዲሁም የእነርሱን ማታለል ለመቋቋም ያዘጋጅዎታል። ይህ አይነ ግልጥ (መገለጥን የሚሰጥ) መጽሐፍ የማስተዋል ችሎታዎን ያሰላል፣ እምነትዎንም ያጠናክራል!
  • ታማኝነት ለመሪዎች የእግዚአብሔር የቅድሚያ መለኪያ ቢሆንም እንኳን ፣በእዚህ ርዕስ የተጻፉ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ በዚህ መጽሐፉ፣ የቤተክርስቲያኖች በመጽናት ማደግን አስመልክቶ በጣም አስፈላጊ መመሪያዎችን በግልፅ ይዘረዝርልናል፡፡ ይህ መጽሐፍ ወቅታዊና ተግባራዊ የሆኑ ርዕሶችን ያካተተ ነው ፣ በመሆኑም ለቤተክርስቲያን መሪዎች የሁልግዜ መገልገያ መሳሪያ ይሆናል፡፡

  • "...ቤቴ እንዲሞላ ወደ መንገድና ወደ ቅጥር ውጣና ይገቡ ዘንድ ግድ በላቸው፤"ሉቃስ 14:23 የእግዚአብሔር የልብ ጩኸት ዓለም እንዲድንና ቤቱ (ቤተ ክርስቲያን) እንድትሞላ ነው! “ትልቅ ቤተ ክርስቲያን” የሚለው ከጋና ትላልቅ ቤተ ክርስቲያኖች የአንዱ መጋቢ የሆኑት የዳግ ሂዋርድ ሚልስ መጽሐፍ የተወለደው ከዚህ መገለጥ ነው፡፡ ይህንን አነሳሽ መጽሐፍ ካነበብክ በኋላ ቤተ ክርስቲያንህ እና አገልግሎትህ ዳግም እንደነበር አይሆንም! “ዶክተር ዳግ ሂዋርድ ሚልስ ለጌታ ለኢየሱስ ክርስቶስ እና ወንጌልን ለዓለም በማዳረስ ውስጥ ላለው ሥራ የተሰጡ ሰው ናቸው፡፡ ታላቅ መሪ እና በአገልግሎት ላሉ ሁሉ አርአያ ናቸው፡፡ እኛም “ቸርች ግሮውዝ

  • ትተውህ የሚሄዱ ሰዎች ሊያጠፉህ ይችላሉ፡፡ ሰዎች ትተውህ በሚሄዱበት ጊዜ ባንተ ላይ የሚመጣብህ መቆዘም፣ ግራ መጋባትና ጭንቀት በቃላት ሊገለፅ አይችልም፡፡ ይህ መጽሐፍ ሰዎች ትተውህ ሲሄዱ ሊያስከትል የሚችለውን ጥፋት እንድትቋቋም የሚረዳህ ነው፡፡ አትሳሳት፡፡ለብቻህ ስትተውና ስትጣል ባንተ አገልግሎት ላይ ብቻ የደረሰ እንዳይመስልህ፡፡ ብዙዎች ይህንን ዓይነት መከራ ተካፍለዋል፡፡ ሰይጣን የመጀመሪያው ዓመፀኛ ነበር ከውድቀቱ ቀን ጀምሮ ብዙ ሰዎች ዓመፀኞች እንዲሆኑ ምክንያት ሆኗል፡፡ ይህን መጽሐፍ በእጅህ ውስጥ በማድረግ ትተውህ በሚሄዱ ሰዎች የሚነሳውን ታማኝ ያለመሆንን መንፈስ ተነስተህ እንድትዋጋው ያደርግሃል፡፡

  • ዛሬ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመገንባት በምናደርገው አጠቃላይ ጥረት ውስጥ ትልቅ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ብዙ ጥቃቅን ነገሮች አሉ። ትንሽ ተጨማሪ ጥረት፣ ጥቂት ተጨማሪ ጊዜ፣ የክርስቶስን ዓላማ ለማስፋፋት የሚውል ጥቂት ተጨማሪ ገንዘብ፣ ላልዳኑ ነፍሳት የሚሰጥ ጥቂት ተጨማሪ ትኩረት እና ለባልንጀራዎ የሚያሳዩት ጥቂት ተጨማሪ እንክብካቤ ትልቅ ለውጥ ያመጣሉ። ጥቂት ተጨማሪ ነገር ማድረግ አይችሉምን? ይህ ችላ ልንለው የማይገባ ጥሪ ነው! ጥቂት ተጨማሪ ነገር ማድረግ አይችሉምን?
  • ትእቢት በብዙ አመታቶች ውስጥ የሰውን ዘር ያጠቃ ገዳይ መርዝ ነው። ትእቢት የማይታ ስለሆነ ትልቅ ሽብር ያስነሳል። ይህን አደጋ ልንዋጋው የምንችለው እንዴት ነው? በትህትና ክትባት ነው! ትህትና ዋነኛ መንፈሳዊ መለኪያ ነው። ስለዚህ ደንቅ ነገር ግን መንፈሳዊ መለኪያ ለምጻፍ የደፈሩ ጥቂቶች ናቸው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ ድብቅ የመሰሉት ትእቢት አጋልጠው ያሳዩናል። እንደኛው በትግል ውስጥ በሚኖር ክርስቲያን የተጻፈው ይህ ድንቅ መጽሐፍ እንደ ህጻን አይነት ትህትና የሆነውን የእየሱስ ክርስቶስ ትህትና እንድታሳድግ ያበረታታሃል እንዲሁም ይባርክሃል።

  • አዝመራው ነጥቷል፣ የነፍሳት መከሩም ደርሷል፤ ይሁን እንጂ ወንጌል ሰባኪዎች ወዴት አሉ? ይህ የዳግ ሂዋርድ ሚልስ አነሳሽ መጽሐፍ ክርስቲያኖች ነፍሳትን ማራኪ እንዲሆኑ አስቸኳይ ጥሪ ያደርጋል፡፡

  • ይህ ጥንታዊ የመስጠት ግንዛቤ አይሁዳውያኖችን ወደ ታዋቂ ሐብት ያደረሳቸው ቢሆንም እንኳን ብዙ ሰዎች ከአሥራት መክፈል አስተሳሰብ ጋር ይታገላሉ፡፡ በዚህ መጽሓፍ ውስጥ ቢሾፕ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ አሥራት መክፈል እንዴት አድርጎ ሐብትን ለማፍራትና የብልጽግናን ተአምራት እንደሚያጠንክር ያስተምረናል፡፡ ከዳግ ሂዋርድ ሚልስ ምርጥ ርዕሶች አንዱ በሆነው በዚህ መጽሐፍ ተባረክ፡፡

Title

Go to Top