• ብዙዎቻችን መልካሙን እና ክፉውን ስለያዘው ዛፍ ብዙ አናውቅም። የምናስበው ለአዳም እና ለሔዋን የደረሰባቸው መጥፎ ነገር ሆኖ እኛ ያመለጥነው ይመስለናል። መልካሙን እና ክፉውን ከያዘው ዛፍ ያመልጥክ ይመስልሃል? በዚህ ቀጥትኛ በሆን መጽሐፍ ወስጥ መልካሙን እና ክፉውን ያዘው ዛፍ እየሰራ እንደሆን ታውቃለህ። አዳምን እና ሔዋንን የፈተናችው ዛሬም ለእኛ እንደዚያው እያቀረበልን እንደሆነ ታውቃለህ። እንደዚሁም በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያልውን እውቅት በመጠቀም በህይወትህና በአገልግሎትህ ውስጥ የሚያልፈውን ነገር እንድታይ ይረዳሃል።

  • አመጸኛ ሰዎች የተደረገላቸውን ነገር አያስታውሱም፣ ብዙ ጊዜም የተወሰኑ ነገሮችን ለመዘንጋት ይመርጣሉ፡፡ ጌታ ለይሁዳ ያደረገለትን ነገር አላስታወሰም፣ ከኢየሱስ ያያቸውንና የሰማቸውንም ነገሮች አላስታወሳቸውም፡፡ አሁን ‘ይሁዳ’ ብለን የምናውቀውን አጸያፊ ባህሪ ያወቅነው ለዚህ ነው፡፡ የማስታወስ ችሎታ አንድ አገልጋይ ሊኖሩት ከሚገቡት እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ መንፈሳዊ ባሕርያት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ የማያስታውሱ ሰዎች፣ ስኬታማ የመሆናቸው እድል እጅግ የጠበበ ነው፡፡ በቀላሉ ወደ ተወሰኑ ከፍታዎች መድረስ ያቅታቸዋል። ይሄ የተለየ እና እምብዛም የማይታወቀው የዚህ መጽሐፍ ርዕሥ፣ ከእግዚአብሔር ለአንተ የተሰጠ ስጦታ ነው

  • ለአገልግሎት መጠራት ለመሪነት መጠራት ነው፡፡ በድጋሚ፣ በቀላሉ በቀረበና ሊተገበር በሚችል አቀራረብ ዶክተር ሂዋርድ ሚልስ ልዩ ክርስቲያን መሪ ያደረጉትን መርሆች ያብራራል፡፡ በዚህ የተገለጠው እውነት ብዙዎችን ለመሪነት ጥበብ ያነሳሳል፡፡

  • በእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ ውስጥ ከመሆን ይበልጥ ጠቃሚ የሆነ ርዕስ የለም፡፡ የወንጌል አገልጋዮችን የሚለያቸው አንድ ነገር ቢኖር የእግዚአብሔርን ድምፅ በትክክል የመስማት ችሎታቸው ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስን ወደ እግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ መከተል እንዴት ጠቃሚ ነገር ነው፡፡ በእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ ውስጥ ስትሆን ታብባለህ ደግሞም ለእግዚአብሔር ማድረግ የምትፈልገውን ሁሉ ከግብ ታደርሳለህ፡፡ ይህ የዳግ ሂዋርድ ሚልስ ድንቅ መፅሐፍ በሕይወትህና በአገልግሎት ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ያደርጋል፡፡

  • እግዚአብሔርን መከተል አስደሳች የአዳዲስ ግኝት ጉዞ ነው፡፡ሌሎችን ሰዎች መከተልና መቅዳት ኢየሱስ ክርስቶስ ዋና የስልጠና ዘዴ አድርጎ የመረጣቸው ጥንታዊ የመማሪያ ጥበቦች ናቸው፡፡ከዚህ በጊዜ ከተፈተነ የስልጠና ዘዴ አፍሮ ከመሸሽ ይልቅ የመከተልን ጥበብ ውበትና ያለበትን ጭምትነት ለመረዳት ጊዜው አሁን ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ማንን፣ ምንን እና እንዴት በሚገባ መከተል እንደሚገባህ ትማራለህ፡፡ይህ የዳግ ሂዋርድ ሚልስ ድንቅ መጽሐፍ ለመከተል ጥበብ በክርስትና ልምምዳችን ውስጥ ተገቢውን ቦታ ይሰጠዋል፡፡

  • ይህ የሚበረታታ መጽሐፍ ነው፡፡ መጋቢ የሆነው ቢሾፕ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ ለምንና እንዴት የመጋቢነትህን አገልግሎት ወጤታማ ማድረግ እንደሚቻል ያስረዳል።

  • ታማኝነት ለመሪዎች የእግዚአብሔር የቅድሚያ መለኪያ ቢሆንም እንኳን ፣በእዚህ ርዕስ የተጻፉ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ በዚህ መጽሐፉ፣ የቤተክርስቲያኖች በመጽናት ማደግን አስመልክቶ በጣም አስፈላጊ መመሪያዎችን በግልፅ ይዘረዝርልናል፡፡ ይህ መጽሐፍ ወቅታዊና ተግባራዊ የሆኑ ርዕሶችን ያካተተ ነው ፣ በመሆኑም ለቤተክርስቲያን መሪዎች የሁልግዜ መገልገያ መሳሪያ ይሆናል፡፡

  • በዚህ ዓይነተኛ መጽሐፍ ውስጥ፣ ቢሾፕ ዳግ ሂዋርድ-ሚልስ የታማኝነት መኖር የመሪውን ብቃት ምን ያህል እንደሚያዳብር ያስተምራሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን፣ የታሪክ እና የሥነ-ጽሑፍ ማጣቀሻዎችን መጠቀማቸው ደግሞ ርዕሰ ጉዳዩ ለማንኛውም ዓይነት መሪ ጠቃሚ እንዲሆን አድርጐታል፡፡

  • በህይወት ጉዞ ውስጥ ስትጓዝ የማይታየው አለም የእውነተኛው እንደሆነና ተፈጥሮዋዊው ደግሞ የማይታየው አለም መገለጥ እንደሆነ ግልጥ እያለ ይታወቅሃል። ግልጥ ያሉ ጠላቶች እንዳሉህ ሁሉ ድብቅ ጠላቶችም አሉህ። ጠላትህን ሳታውቀው፤ ስልቱን ሳትረዳ፤ አሰራሩን እና መሳሪያውን ሳታውቅ ልትዋጋው ትችላለህን? ለህይወትህ ጉዞ ይህ መጽሐፍ ዋነኛ ነው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የማይታየው ጠላትህ ማን እንደሆነ፤ የህልውናቸው ስር መሰረት፤ ባህሪያቸው እና እንዴት እንደምታሸንፋቸው ትማራለህ።ይህ ውድ መጽሐፍ የማይታዩትን ጠላቶችህን እንድትቋቋማቸው ይርዳህ!

  • የቤተ ክርስቲያን እድገት አስቸጋሪና የማይጨበጥ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ሁሉም መጋቢዎች ቤተ ክርስቲያኖቻቸው እንዲያድጉ ይፈልጋሉ፡፡ ይህ መጽሐፍ ስለ ቤተ ክርስቲያን እድገት ላለህ ጥያቄህ መልስ ይሆናል፡፡የቤተ ክርስቲያንን እድገት ለማየት እንዴት “ብዙ ነገሮች በአንድ ላይ እንደሚሰሩ " ትረዳለህ፡፡ ውድ መጋቢ፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉት ቃሎችና ቅባቱ በልብህ ውስጥ ሲገቡ፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን እድገት ትጸልይ የነበረውን በገሀድ ታየዋለህ፡፡

  • የቅባቱ ቦታው የተቀባው ሰው ጋር ነው። ቅባት ከተቀባው ሰው ጋር አይለያይም። ቅባቱ በእግዚአብሔር ሰው ውስጥ ነው! ቅባቱ ከእግዚአብሔር ሰው ጋር ነው! ቅባቱ በእግዚአብሔር ሰው ላይ ነው! ይህ በዳግ ሂዋርድ ሚልስ የተጻፈው ማራኪ አዲስ መጽሐፍ ቅባቱን ለሚፈልጉ ሁሉ ልባቸውን ቅባቱ ወዳለበት የሚጎትት ነው።

  • በእርግጥ እግዚአብሔር ብዙ ሰዎችን ጠርቷል፡፡ በእዚህ ምድር ላይ ያለን ሕይወት እግዚአብሔርን ለማገልገል የተሰጠን ዕድል ሲሆን የእርሱም ዓይኖች ለመንግሥቱ በምንሠራቸው ነገሮች ላይ ናቸው፡፡ ይህ መጽሐፍ ሲነበብ ያነቃቃል፡፡ በጸሐፊው የተላለፈውን መልእክት ብትቀበል፣ የሕይወትህን መልካም አጋጣሚዎች በአግባቡ እንድትጠቀምባቸው የሚረዳህን ጥበብ ትቀበላለህ፡፡

Title

Go to Top