-
በመላው ዓለም ልጆች "አመሰግናለሁ" ማለትን ይማራሉ። ጥናቶች እንደሚያሳዩት "አመሰግናለሁ" ማለት ገና በለጋ ዕድሜያችን በውስጣችን የሰረጸ ነገር ነው። ሆኖም ግን መጽሐፍ ቅዱስ በመጨረሻው ዘመን ሰዎች የማያመሰግኑ እንደሚሆኑ ይናገራል! በታዋቂው ደራሲ ዳግ ሂዋርድ-ሚልስ የተዘጋጀው ይህ ግሩም ሥራ እንዴት አመስጋኝ ሆነን መቆየት እንደምንችል ያስተምረናል፤ እንዲሁም ምስጋና ለማይሰጡ ሰዎች ምን እንደሚከሰት ይገልጻል። እነዚህን የተቀቡ ገጾች ሲመለከቱ ይባረካሉ፣ እንዲሁም ከአመስጋኞች መካከል ለመሆን ይበረታታሉ። -
እግዚአብሔርን ማገልገል ትልቅ ነገር እንደሆን ሰምተህ ልታውቅ ትችላለህ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ማገልገል እንዴት ትልቅ ነገር እንደሆነ ጠለቅ ብልህ አስበህ ላታውቅ ትችላለህ። በዚህ ለየት ባልው የዳግ ሂዋርድ ሚልስ መጽሕፍ ውስጥ ማን የእግዚአብሔር አግልጋይ እንደሆነ እና እንዴት እግዚአብሔርን ማገልገል እንዳለብህ ትረዳለህ። እግዚአብሔርን ብሚያገለግሉት እና እግዚአብሔርን በማያገልግሉት መካክል ያልው ልዩነት ግልጽ ባለው መንገድ ይብራልህ! እግዚአብሔርን ክሚያገለግሉት ውስጥ የምትቆጠር ሁን! -
እግዚአብሔር ሕዝቡን ለማብዛትና እንደ መንጋ እንዲጨምሩ ለማድረግ ታላቅ ዕቅድ አለው። የእግዚአብሔር ዕቅድ ሕዝቡ ጥቂትና ደካማ እንዳይሆኑ ነው፤ ይህ ለእርስዎ ያለው የእግዚአብሔር ዕቅድ ነው። የቤተክርስቲያን ዕድገት ሊታሰብ የሚችል መሆኑን ጠይቀው ያውቃሉ? ያልሠሩ ብዙ ስልቶችን ሞክረዋል? ሲጠብቁት የነበረው መጽሐፍ ይህ ነው! እዚህ የተጻፉትን እያንዳንዱን የትንቢት ቃላት ተቀበሉ፣ በሕይወትዎና በአገልግሎትዎ ላይም እንደሚፈጸሙ እመኑ። ይህ መጽሐፍ ለ "ቤተክርስቲያን ዕድገት" ስብስብዎ ሌላው አስፈላጊ መጽሐፍ ሲሆን፣ ደራሲው ራሱ የተጠቀሙባቸውንና የማይካድ ውጤት ያመጡ ስልቶችን በመጠቀም አገልግሎትዎን ወደ ድርብ እና ታላቅ ሚሲዮናዊ ቤተክርስቲያን ደረጃ ያሸጋግረዋል! -
በዚህ ምድር ላይ ያለው ሕይወት በተለያዩ ነገሮች ይነካል። ለስኬት ያን ያህል ጥረት ቢያደርጉም፣ ሕይወት ለምን ባልተጠበቁ ውጤቶች የተሞላ እንደሆነ ጠይቀው ያውቃሉ? ለምናደርጋቸው ነገሮች ውጤት ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ምክንያቶች፣ አካላት፣ እንዲያውም ወሳኝ ነገሮች (determinants) አሉ። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ፣ የእያንዳንዱን ሰው መንገድ የሚያቋርጡ ወሳኝ ነገሮችን ያገኛሉ።
ይህ መጽሐፍ በሕይወት ሩጫ ውስጥ ምርጡን ውጤት እንዲያመጡ ዕድል ይሰጥዎታል! “ጊዜና እድልም ሁሉንም ያገኙታል” የሚለውን ተረድቶ እንደሚራመድ ሰው፣ በዚህ መጽሐፍ መገለጥ ይመሩ! እነዚህ ወሳኝ ነገሮች ሕይወትዎን ወደፊት ያራምዱት!
-
ብዙ ክርስቲያኖች ከእግዚአብሔር ጋር በሚያደርጉት ዕለታዊ ጉዞ ውስጥ የመገናኛው ድንኳን ያለውን ጠቀሜታ አያውቁም። ብዙዎቻችን የመገናኛውን ድንኳን የተለያዩ ገጽታዎች አንረዳም። በእርግጥም፣ ብዙዎቻችን እግዚአብሔር ድንኳኑን ለመገንባት ለሰጣቸው ዝርዝር መመሪያዎች እንገረማለን። መገናኛው ድንኳን ለእግዚአብሔር መገኘት ተብሎ በጥንቃቄ የተገነባ፣ ምስጢራዊ አካባቢ ነበረ። በዚህ ጥልቅ ጥናት ውስጥ፣ በእግዚአብሔር መገናኛ ድንኳን ውስጥ ጉዞ እናደርጋለን። የመገናኛውን ድንኳንና የእግዚአብሔርን በሰዎች መካከል መገኘት እንድንረዳ ማህተሞቹ ተከፍተዋል። -
ይህን እጅግ አስፈላጊ ጥያቄ ቆም ብለህ ጠይቀህ ታውቃለህ? "የሞቱ ሰዎች ሁሉ የት ሄዱ?" እውነታው ይህ ነው፣ ከመቃብር ማዶ ሁለት መዳረሻዎች ብቻ አሉ፤ ገነት እና ገሃነም! በክርስቶስ ጻድቅ የሆኑ ሰዎች መንፈስ ከአብ ጋር ወደ ሰማይ ይሄዳል፣ ኢየሱስ ክርስቶስን ያልተቀበሉ ሰዎች መንፈስ ግን ወደ ገሃነም ይጣላል። ይህ በብዙ ሽያጭ የታወቀው ደራሲ ዳግ ሄዋርድ-ሚልስ ያዘጋጀው አስደናቂ መጽሐፍ ገሃነምን በማንኛውም ዋጋ ማስወገድ እንዳለብህ ምንም ጥርጣሬ አይተውልህም። በገሃነም ውስጥ እውነተኛ ሰዎች አሉ! ከገሃነም ማምለጥ አለብህ! ዳግም መወለድ አለብህ! ሌላ አማራጭ የለም! -
የማይጠማውን ሰው እንዲጠጣ ማድረግ በጣም አስቸጋሪ ነው ። መጠጣት ከመቻሉ በፊት ጥማት መኖር አለበት ። የማይጠሙ ሰዎች መጠጥን እንኳ አይጠይቁም ። ለእግዚአብሔር ያለዎት ረሀብና ጥማት ወደ ጥልቁ ለመሄድ ጉዞዎን ሊያስጀምርዎት ይችላል ። ጥልቅ በሆነው ነገር ውስጥ እንዲገቡና የበለጠ እንዲያደርጉ የሚያደርጋችሁ ያላችሁ ጥልቅ ፍላጎት ነው! ለበለጠ ነገር ጥማት ያላቸው ብቻ ወደ ጥልቁ መሄድ ይችላሉ ። በእግዚአብሔር ነገሮች ውስጥ ወደ ጥልቁ መሄድ ብዙ ጥቅሞች አሉት ። በእግዚአብሔር ውስጥ ወደ ጥልቁ ከሄዱ፣ እጅግ የላቀውን የጌታን ታላቅነት ሲለማመዱ ራስዎን ያገኙታል ። ወደ ጥልቁ ከሄዱ፣ የበለጠ ያደርጋሉ! የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገሮች ለመለማመድ ትፈልጋላችሁ? ። እንደምትፈልጉ እርግጠኛ ነኝ፣ ይህን የሚያረካ መጽሐፍ እያነበባችሁ ያላችሁትም ለዚህ ነው ። “ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና” የሚለውን ቃል አስታውሱ ። ወደ ጥልቁ ስትገቡና የበለጠ ስታደርጉ ተሞልታችሁ ይሁን!