• ወደኋላ ማፈግፈግ፣ ያልተለመደ ርዕስ ቢሆንም፣ በክርስቲያኖች መካከል ተዘውትሮ ስለሚታይ ክስተት ያስተምረናል፡፡ ብዙዎች ይጀምራሉ፤ እስከፍጻሜ ድረስ የሚጸኑት ግን ብዙዎች አይደሉም፡፡ በዚህ መጽሐፍ ላይ ቢሾፕ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ ደውሉን ያሰማል፣ እንዳንዱ ክርስቲያንም ለምን ለመንግሥተ ሰማይ መብቃት እንዳለበት በግልጽ ያሳያል !

  • ለመጋቢዎች እና ለመጋቢዎች ሚስቶች የተለየው መጽሐፍ በመጨረሻ ይኸው መጣ! መጋቢዎች ወይም የመጋቢዎች ሚስቶች ካልሆናችሁ ይህ መጽሐፍ አይመለከታችሁመ! ይህን ምጽሐፍ ለማንበብ መስፈርቱን ካሟላችሁ እግዚአብሔር በዚህ ሃሳብን ከውስጥ በሚፈትሸው መጽሐፍ ወስጥ ይናገራችሁ። በየገጾቹ ሚስቶች በመጋቢዎች ህይወት ውስጥ የሚጫወጡት ሚስጥራዊ ሚና ይገለጣል። በየግጾቹ እየታነጻችሁ ወደ በረከታቸሁ ይምሩቿሁ።

  • ብዙዎቻችን መልካሙን እና ክፉውን ስለያዘው ዛፍ ብዙ አናውቅም። የምናስበው ለአዳም እና ለሔዋን የደረሰባቸው መጥፎ ነገር ሆኖ እኛ ያመለጥነው ይመስለናል። መልካሙን እና ክፉውን ከያዘው ዛፍ ያመልጥክ ይመስልሃል? በዚህ ቀጥትኛ በሆን መጽሐፍ ወስጥ መልካሙን እና ክፉውን ያዘው ዛፍ እየሰራ እንደሆን ታውቃለህ። አዳምን እና ሔዋንን የፈተናችው ዛሬም ለእኛ እንደዚያው እያቀረበልን እንደሆነ ታውቃለህ። እንደዚሁም በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያልውን እውቅት በመጠቀም በህይወትህና በአገልግሎትህ ውስጥ የሚያልፈውን ነገር እንድታይ ይረዳሃል።

  • አመጸኛ ሰዎች የተደረገላቸውን ነገር አያስታውሱም፣ ብዙ ጊዜም የተወሰኑ ነገሮችን ለመዘንጋት ይመርጣሉ፡፡ ጌታ ለይሁዳ ያደረገለትን ነገር አላስታወሰም፣ ከኢየሱስ ያያቸውንና የሰማቸውንም ነገሮች አላስታወሳቸውም፡፡ አሁን ‘ይሁዳ’ ብለን የምናውቀውን አጸያፊ ባህሪ ያወቅነው ለዚህ ነው፡፡ የማስታወስ ችሎታ አንድ አገልጋይ ሊኖሩት ከሚገቡት እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ መንፈሳዊ ባሕርያት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ የማያስታውሱ ሰዎች፣ ስኬታማ የመሆናቸው እድል እጅግ የጠበበ ነው፡፡ በቀላሉ ወደ ተወሰኑ ከፍታዎች መድረስ ያቅታቸዋል። ይሄ የተለየ እና እምብዛም የማይታወቀው የዚህ መጽሐፍ ርዕሥ፣ ከእግዚአብሔር ለአንተ የተሰጠ ስጦታ ነው

  • ብዙ ሰዎች የወጣትነት ዘመናቸው ዝም ብሎ በመታለልና ጨዋታ በመጫወት ማለፍ እንዳለበት ያስባሉ። የእግዚአብሔር ነገሮች የተሰሩት በዚህ ዓለም ውስጥ ለቆዩ፣ ብዙ አሳዛኝ ቀናትን ላሳለፉ፣ በዕድሜ ለገፉ፣ ይበልጥ ረጋ ላሉ፣ በሳልና ልምድ ላላቸው ሰዎች እንደሆነ ያስባሉ። ዳግ ሂዋርድ-ሚልስ የወጣቶች ተሟጋች ናቸው። ወጣቶች ለእግዚአብሔር ለመሥራትና እርሱን በሚቻል በላቀ መንገድ ለማገልገል እጅግ ብቁ እንደሆኑ በጽኑ ያምናሉ። ይህ ድንቅ መረጃ ሰጭና አስተማሪ መጽሐፍ፣ በሃያ ዓመት ዕድሜህ (Ready @ 20) ልታደርጋቸው በሚገቡ ብዙ ነገሮች ውስጥ ይወስድሃል! ዕድሜህ ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ ነው? እንግዲያውስ የጌታን ሠራዊት ለመቀላቀል ዝግጁ ነህ።
  • ለአገልግሎት መጠራት ለመሪነት መጠራት ነው፡፡ በድጋሚ፣ በቀላሉ በቀረበና ሊተገበር በሚችል አቀራረብ ዶክተር ሂዋርድ ሚልስ ልዩ ክርስቲያን መሪ ያደረጉትን መርሆች ያብራራል፡፡ በዚህ የተገለጠው እውነት ብዙዎችን ለመሪነት ጥበብ ያነሳሳል፡፡

  • በእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ ውስጥ ከመሆን ይበልጥ ጠቃሚ የሆነ ርዕስ የለም፡፡ የወንጌል አገልጋዮችን የሚለያቸው አንድ ነገር ቢኖር የእግዚአብሔርን ድምፅ በትክክል የመስማት ችሎታቸው ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስን ወደ እግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ መከተል እንዴት ጠቃሚ ነገር ነው፡፡ በእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ ውስጥ ስትሆን ታብባለህ ደግሞም ለእግዚአብሔር ማድረግ የምትፈልገውን ሁሉ ከግብ ታደርሳለህ፡፡ ይህ የዳግ ሂዋርድ ሚልስ ድንቅ መፅሐፍ በሕይወትህና በአገልግሎት ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ያደርጋል፡፡

  • እግዚአብሔርን መከተል አስደሳች የአዳዲስ ግኝት ጉዞ ነው፡፡ሌሎችን ሰዎች መከተልና መቅዳት ኢየሱስ ክርስቶስ ዋና የስልጠና ዘዴ አድርጎ የመረጣቸው ጥንታዊ የመማሪያ ጥበቦች ናቸው፡፡ከዚህ በጊዜ ከተፈተነ የስልጠና ዘዴ አፍሮ ከመሸሽ ይልቅ የመከተልን ጥበብ ውበትና ያለበትን ጭምትነት ለመረዳት ጊዜው አሁን ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ማንን፣ ምንን እና እንዴት በሚገባ መከተል እንደሚገባህ ትማራለህ፡፡ይህ የዳግ ሂዋርድ ሚልስ ድንቅ መጽሐፍ ለመከተል ጥበብ በክርስትና ልምምዳችን ውስጥ ተገቢውን ቦታ ይሰጠዋል፡፡

  • ይህ የሚበረታታ መጽሐፍ ነው፡፡ መጋቢ የሆነው ቢሾፕ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ ለምንና እንዴት የመጋቢነትህን አገልግሎት ወጤታማ ማድረግ እንደሚቻል ያስረዳል።

  • ታማኝነት ለመሪዎች የእግዚአብሔር የቅድሚያ መለኪያ ቢሆንም እንኳን ፣በእዚህ ርዕስ የተጻፉ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ በዚህ መጽሐፉ፣ የቤተክርስቲያኖች በመጽናት ማደግን አስመልክቶ በጣም አስፈላጊ መመሪያዎችን በግልፅ ይዘረዝርልናል፡፡ ይህ መጽሐፍ ወቅታዊና ተግባራዊ የሆኑ ርዕሶችን ያካተተ ነው ፣ በመሆኑም ለቤተክርስቲያን መሪዎች የሁልግዜ መገልገያ መሳሪያ ይሆናል፡፡

  • ክብር እያንዳንዱ ሰው ሊያውቀው የሚገባ ጠቃሚ ነገር ነው። ክብርን መስጠት የመጽሐፍ ቅዱስ ትእዛዝ ነው። ከእግዚአብሔር ጋር ባለዎት ግንኙነት ውስጥ ክብር በጣም አስፈላጊ ነው። ከነቢይዎ፣ ከፓስተርዎ፣ ከባልዎ እና ከሌሎች የሥልጣን አካላት ጋር ባለዎት ግንኙነት ውስጥም ክብር ትልቅ ቦታ አለው። ክብር ለሚገባው ሰው ክብር ካልሰጡ፣ ከተወሰኑ ሰዎች ጋር ሊኖርዎት የሚገባው ትክክለኛ ግንኙነት ሊኖራችሁ አይችልም። ይህ ለሕይወት መመሪያ የሚሆን መጽሐፍ ነው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ለአንድ ሰው እንዴት ክብር መስጠት እንደሚቻል፣ የአለመከበር ምልክቶች፣ የክብር ዋጋ እና ሌሎች ብዙ ነገሮችን ይማራሉ። ይህ መጽሐፍ አስፈላጊ የሆኑ ግንኙነቶችዎን ለመጠበቅ የሚረዱ ቁልፎችን ይዟል። በክብር ረገድ ጎድለው እንዳይገኙ ምኞቴ ነው!
  • የቤተክርስቲያን ዕድገት ስለመቻሉ አስበህ ታውቃለህ? ያልሠሩ ብዙ የስትራቴጂ መንገዶችን ሞክረሃል? ስትጠብቀው የነበረው መጽሐፍ ይህ ነው! በዚህ ውስጥ የተጻፈውን እያንዳንዱን የትንቢት ቃል ተቀበል፣ በሕይወትህና በአገልግሎትህ ላይ እንደሚፈጸሙም እመን! ስትጠብቀው የነበረው መጽሐፍ ይህ ነው! በዚህ ውስጥ የተጻፈውን እያንዳንዱን የትንቢት ቃል ተቀበል፣ በሕይወትህና በአገልግሎትህ ላይ እንደሚፈጸሙም እመን!

Title

Go to Top