-
መጽሐፍ ቅዱስ ስለተለያዩ የደም ዓይነቶች ይናገራል፤ የፍየሎች ደም፣የበጎች ደም፣የእርግቦች ደም! እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር ካለ ደም ሥርየት የለም ይላል። በመሆኑም እነዚህ የተለያዩ የደም ዓይነቶች ኃጢያታችንን ያስወግዱልናልን? መልሱ ግልጽ የሆነ አይደለም ነው። ታዲያ ኃጢያታችን ሊያስወግድልን የሚችል ምንድ ነው? ከኢየሱስ ክርስቶስ ደም ሌላ ምንም የለም! ኃጢያታችን ሊያስወግድ እና ድነትን ሊሰጠን የሚችለው የኢየሱስ ደም ብቻ ነው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ስለኢየሱስ ክርስቶስ ደም ብዙ የተቀደሱ እውነታዎችን ታገኛለህ። የኢየሱስ ደም እንዴት ህይወት እንደሚሰጥና እንዴት ትልቅ ዋጋ ያለው እንደሆነም ትደርስበታለህ። እንዲሁም በመን -
በእምነት ርዕሰ ጉዳይ ላይ የቀረበው ይህ አስደሳችና ጥልቅ ጥናት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው ትኩረት የሚስብ መሆኑ እርግጥ ነው። ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው፣ ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም። እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ለሚፈልግ እያንዳንዱ ሰው ይህ መጽሐፍ የግድ መነበብ ያለበት ለዚህ ነው። እምነት አብርሃምን የእግዚአብሔር ወዳጅ ካደረገው፣ እምነት ከእግዚአብሔር ጋር በምናደርገው ጉዞ ውስጥ በጣም አስፈላጊ ነው። ይህ መጽሐፍ ሀብት ነው! በእምነት ለመመላለስና ለመኖር የሚያስፈልጉ ምስጢሮችን ያግኙ። በሕይወትዎ ውስጥ የማይቻለውን ነገር ለማሳካት የሚያስፈልጉዎትን የእምነት ምስጢሮች ይግለጡ! -
ያለ ምንም ጥርጥር፣ የሚዘጋጁ ሰዎች ካልተዘጋጁት የተለዩ ናቸው። ዝግጅት ማለት እራስን ከፊት ለሚጠብቅ ተግባር ማዘጋጀት ማለት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁሉ፣ ለሚመጣው ነገር እንድንዘጋጅና እራሳችንን ዝግጁ እንድናደርግ ተነግሮናል። የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈጸም ዝግጁ መሆንዎን ለማረጋገጥ የሚወስዱትን እያንዳንዱን እርምጃ እግዚአብሔር ይመለከታል። ጌታን ለማገልገል ያለዎት ዝግጁነት በእርስዎ ዝግጅት ላይ የተመካ ነው! እግዚአብሔርን ለመገናኘት እንኳን ዝግጅት እንደሚያስፈልገን ልብ ይበሉ! በዚህ በጉጉት ሲጠበቅ በነበረው የዳግ ሂዋርድ-ሚልስ (Dag Heward-Mills) መጽሐፍ፣ እግዚአብሔር ለጠራዎት ለበጎ ሥራዎች ሁሉ እንዴት በዝግጁነትና በዝግጅት ሁኔታ ውስጥ መኖር እንደሚችሉ ይመራሉ። በዚህ መጽሐፍ አማካኝነት የተለዩ ለመሆን ተቃርበዋል! -
ዳግ ሂዋርድ ሚልስ፣ በርካታ ተፈላጊ መጽሐፍ የጻፉና ከእነዚሁም ውስጥ “ታማኝነትና ታማኝ አለመሆን” የተባለው በዓለም ላይ ታዋቂ በሆነውን መጽሐፋቸው ይታወቃሉ። በአሁኑ ጊዜ ዩናይትድ ዲኖምኔሽን ኦርጂኔትድ ፍሮም ዘ ላይትሃውስ ግሩፕ ኦፍ ቸርች (United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches) ተብሎ የሚጠራው ቤተ ክርስቲያን መስራች ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሶስት ሺህ ቤተክርስቲያኖች አሉት። ዳግ ሂዋርድ ሚልስ፣ በዓለማቀፍ ደረጃ ወንጌላዊ ሲሆኑ “ፈዋሹ ኢየሱስ ክሩሴድ (HEALING JESUS CRUSADE) ” በተሰኘው እና በአለም ዙሪያ በተለያዩ ኮንፈረንሶች ላይ በአገልግሎታቸው ይታወቃሉ፡፡ ይበልጥ መረጃ ከፈለጉ ድህረ ገጻቸውን ይጎብኙ፣ www.daghewardmills.org. -
ክፋት በመላው ዓለም እንደሚገኘው ሁሉ፣ ዕብደትም በምድር ላይ በእኩል ተሰራጭቷል፤ ቤተ ክርስቲያንም ከዚህ የተለየች አይደለችም — የአእምሮ ጤና ችግሮች ዛሬ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በስፋት ይስተዋላሉ! ከዚህ ቀደም ጤናማ የነበሩ ሰዎች ዕብደት ሳይታወቅና ሳይመረመር በመቅረቱ ምክንያት ወደ ፀረ-ማኅበራዊ፣ ምክንያታዊ ያልሆነ እና እጅግ ሞኝነት ወደ ተሞላበት ባሕርይ ሲበታተኑ ማየት አሳዛኝ ነው። በዚህ ድንቅ መጽሐፍ ውስጥ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቁት ደራሲ ዳግ ሄዋርድ-ሚልስ፣ የተለያዩ የአእምሮ ጤና ችግሮችን ዓይነቶች እና ከዛሬዋ ቤተ ክርስቲያን ጋር እንዴት እንደሚዛመዱ ያብራራሉ፤ ማንኛውም ተራ ሰው ሊያደንቀውና ሊረዳው በሚችል ቀላል መንገድ ቀርቧል። በእርግጥም ዕብደትን ለይቶ ማወቅ መቻል ማስተዋል ባለው ሰው ውስጥ ርኅራኄን ያነሳሳል። -
ብዙ ተስፋ የቆረጡ ፓስተሮች ይህን ጥያቄ ለራሳቸው ጠይቀዋል፡ "ይህች ቤተ ክርስቲያን ለምን አትሠራም?" ከዚህ ጥያቄ ጋር ትተዋወቃለህ፣ አይደል? አዲስ የተሾምክ ፓስተር ልትሆን ትችላለህ፣ ለብሔራት የተላክ ሚስዮናዊ ልትሆን ትችላለህ፣ የተሳካለት ቤተ ክርስቲያን ቅርንጫፍ የምትጀምር ፓስተር ልትሆን ትችላለህ… ዝርዝሩ ይቀጥላል! ይህ ከእኛ ብዙዎቻችን መልስ የሚያስፈልገን ጥያቄ ነው። በተለመደው ተግባራዊ፣ ቀጥተኛ እና ምድራዊ አቀራረቡ፣ በብዙ ሽያጭ የታወቁት ደራሲ ዳግ ሄዋርድ-ሚልስ፣ ለረጅም ጊዜ መልስ ሲፈልግ የቆየውን ጥያቄ ይመልሳሉ። ይህ መጽሐፍ ቤተ ክርስቲያን ለሚመራ ማንኛውም ሰው፤ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለማካፈል እና ሕዝብን ወደ እግዚአብሔር ለመሰብሰብ ፍላጎት ላለው ማንኛውም ሰው የግድ ሊነበብ የሚገባው መጽሐፍ ነው። -
ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ፥ በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት። እናንተ ግን ይቅር ባትሉ በሰማያት ያለው አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም። (ማር.11:25-26) እነዚህን ሁለት ጥቅሶች ማድረግ ያንቀጠቅጥሃል? ከሆነ መፍተሄው እዚህ አለልህ። በዚህ በጣም አስፈላጊ በሆነው መጽሐፍ ውስጥ በቀላሉ ይቅር ማለትን ትማራለህ፤ እንደዚሁም የሰማዩ አባትህን ይቅርታ ትጠግባለህ። በቀላሉ እና ከልብህ ይቅር ማለት እስክትችል ድረስ ይህ መጽሐፍ አብሮህ ይኑር። -
በድሮ ጊዜ የነበሩት ነቢያቶች ለኛ የትገለጠውን ታላቁን ድነት አጥብቀው ይፈልጉት እንደነበር ታውቃለህ?ይህ ድነት ለሰው ልጆች እንዴት እንደሚደርስ መገመት አይችሉም ነበር…እኛ ግን ይህን ድነት ለመቀበል ታድለናል። ድነትን የተቀበልነው አንድ ሰው ስለነገረን ንው። በዚህ ድንቅ መጽሐፍ ወንጌላዊው ዳግ ሂዋርድሚልስ ታላቁን መዳናቸንን እንድንረዳ ብቻ ሳይሆን፤ እንዴትም አድርግን ይህንን ታላቅ የድነት ወንጌል ለሌሎች ማካፈል እንደምንችል ያሳዩናል። ሁላችንም የወንጌላዊን ስራ የምንሰራ እንሁን! -
አዲስ ሰው (ኖቪስ) ለአንድ ነገር አዲስ የሆነ ነው፤ እርሱ ጀማሪ ነው። እግዚአብሔር አዲስ የተሾመ ወይም አዲስ የተፈጠረ አካል አይደለም። ስለ እግዚአብሔር አዲስ የሚያደርገው ምንም ነገር የለም። እርሱ መጀመሪያ ነው! እግዚአብሔር ለዘላለም የነበረ ነው። እርሱ ሁሉን የሚችል ጌታ አምላክ፣ የዘላለም ጌታ ነው። እኛ ግን አዲስ ሰዎች (ኖቪሶች) የመሆን ዕድላችን ሰፊ ነው። በየቀኑ አዳዲስ ግኝቶችን የምናገኝ እኛ ነን። አዲስ ሰው እንደ ትዕቢት ላሉ ለብዙ አደጋዎች የተጋለጠ ነው። አዲስ ሰው ለዓመታት ለተመሠረቱ ሥልጣናት ራሱን ከፍ አድርጎ እንዲያነሳ የሚያደርገው የአዲስ ሰው ኩራት ነው። ሉሲፈር በትዕቢቱ ምክንያት የተፈረደበት አዲስ ሰው ነበረ! እርሱም በ**«በዲያብሎስ ፍርድ»** ውስጥ ወደቀ። የሉሲፈር ትልቁ ስህተት ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጻጸር ስለራሱ ትክክለኛ ግምት ያልነበረው መሆኑ ነው። በእነዚህ ሐሳብ ቀስቃሽ ምዕራፎች ውስጥ፣ ስለ አዲስ ሰው ኩራት የቀረቡትን ትምህርቶች በሙሉ ጥንቃቄ ትወስዱ ዘንድ ይሁን፤ ያለበለዚያ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሱትን ነጥቦች ሁሉ ለራሳችሁ ጥፋትና ፍርድ ትፈጽማላችሁ። ከአዲስ ሰው አደጋዎች ሁሉ ነፃ ውጡ!