-
"...ቤቴ እንዲሞላ ወደ መንገድና ወደ ቅጥር ውጣና ይገቡ ዘንድ ግድ በላቸው፤"ሉቃስ 14:23 የእግዚአብሔር የልብ ጩኸት ዓለም እንዲድንና ቤቱ (ቤተ ክርስቲያን) እንድትሞላ ነው! “ትልቅ ቤተ ክርስቲያን” የሚለው ከጋና ትላልቅ ቤተ ክርስቲያኖች የአንዱ መጋቢ የሆኑት የዳግ ሂዋርድ ሚልስ መጽሐፍ የተወለደው ከዚህ መገለጥ ነው፡፡ ይህንን አነሳሽ መጽሐፍ ካነበብክ በኋላ ቤተ ክርስቲያንህ እና አገልግሎትህ ዳግም እንደነበር አይሆንም! “ዶክተር ዳግ ሂዋርድ ሚልስ ለጌታ ለኢየሱስ ክርስቶስ እና ወንጌልን ለዓለም በማዳረስ ውስጥ ላለው ሥራ የተሰጡ ሰው ናቸው፡፡ ታላቅ መሪ እና በአገልግሎት ላሉ ሁሉ አርአያ ናቸው፡፡ እኛም “ቸርች ግሮውዝ
-
ቤተ ክርስቲያናትን መትከል ካሪዝማቲክ በሆኑ አገልጋዬች ዘንድ በሰፊው የተለመደ ክስተት ነው፡፡ የቀደምት ደቀ መዛሙርት ዋና እንቅስቃሴ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ስኬታማ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ለማካሄድ በርካታ ጭብጦችን ያካተተ ክህሎትን ይጠይቃል፡፡ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ፣ በመላው ዓለም ከ 1200 በላይ አጥቢያዎች ያሏት ቤተ ክርስቲያን መስራችና መጋቢ ሲሆኑ፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተለያዮ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ግብአቶችን ይተነትናሉ፡፡ ይህ መጽሐፍ ቤተ ክርስቲያን መትከልን የሕይወት ግቡ ማድረግ ለሚፈልግ አገልጋይ የስልጠና ማንዋል ነው።
-
ቅባት ወደ ተሳካ እና ፍፃሜው ያማረ አገልግሎት ውስጥ ለመግባት የሚያስፈልግ ዋነኛ ቁልፍ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች በፍጹም ቅንነት በራሳቸው ጥረት የእግዚአብሔርን ሥራ ለመሥራት ሞክረው መንገድ ቀርተዋል፡፡ እነኚህ ሰዎች ያልተገነዘቡት ነገር “በመንፈሴ (በቅባት) እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም” (ዘካሪያስ 4፡6) የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርህ ነው፡፡ “ይህ ቅባቱን ያዝ” በሚል ርዕስ በቢሾፕ ዳግ ሂዋርድ-ሚልስ የተጻፈ ልዩ መጽሐፍ ቅባቱን መያዝ ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና እንዴት ተደርጐ እንደሚያዝም ተግባራዊ በሆነ መልኩ ያስተምራል ! የዚህን መጽሐፍ ገጾች ስታነብ በውስጥህ ቅባቱን የመያዝ መሻትህ ይቀጣጠል !