ዳግሂዋርድሚልስ፣በርካታተፈላጊመጽሐፍየጻፉናከእነዚሁምውስጥ“ታማኝነትናታማኝአለመሆን” የተባለውበዓለምላይታዋቂበሆነውንመጽሐፋቸውይታወቃሉ።በአሁኑጊዜዩናይትድዲኖምኔሽንኦርጂኔትድፍሮምዘላይትሃውስግሩፕኦፍቸርች(United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches) ተብሎየሚጠራውቤተክርስቲያንመስራችናቸው፡፡በአሁኑጊዜሶስትሺህቤተክርስቲያኖችአሉት።
ዳግሂዋርድሚልስ፣በዓለማቀፍደረጃወንጌላዊሲሆኑ“ፈዋሹኢየሱስክሩሴድ(HEALING JESUS CRUSADE) ” በተሰኘውእናበአለምዙሪያበተለያዩኮንፈረንሶችላይበአገልግሎታቸውይታወቃሉ፡፡ይበልጥመረጃከፈለጉድህረገጻቸውንይጎብኙ፣www.daghewardmills.org.

  • ኢየሱስ ክርስቶስ ብልጽግናንና ሀብትን የሚገዛውን አስደንጋጭ መርህ ገልጦልናል፡፡ ያለው ይበልጥ ይኖረዋል! እንዴት አግባብ ያልሆነ ነገር ይመስላል! ሆኖም ግን በየእለቱ በፊታችን የሚሆነው ነገር ይህ እውነታ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ ጥቂት የተረዳነውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ለማብራራት ይሞክራል፡፡ ይህንን የዳግ ሂዋርድ ሚልስ አዲስ መጽሐፍ ስታጠና ስለ ብልጽግናም ምሥጢራት ታላላቅ እይታዎችን ትቀበላለህ፡፡

  • ላይኮስ የሚለው የግሪክ ትርጉሙ ክህሎት የሌለው ማለት ነው፡፡ታሪክ በተደጋጋሚ 'ልዩ ክህሎት' ባልተጎናጸፉ ሰዎች ታላላቅ ሁነቶች እንደተከወኑ ያስተምረናል በትርፍ ጊዜያቸው የሚገለግሊ ሰዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ የማይሰሩ ከሆነ፣ ሸክምን በትርፍ ጊዜያቸው ለሚያገለግሉ ሰዎች ማካፈል እና ለምን የትርፍ ጊዜ አገልግሎትን ለመጠበቅ መዋጋት እንዳለብን በዚህ የዳግ ሂዋርድ ሚልስ ዓይነተኛ መጽሐፍ አማካኝነት ተማር፡፡

  • መጽሐፍ ቅዱስ በፊሊጵስዮስ ፪፡፬ ላይ “እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ።” ይላል። በዚህ ይጊዜው መጽሐፍ ውስጥ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ ከራስህ ማሰብ አልፈህ ስለሌሎች ማስብ እንድትጀምር ያበረታታሃል። ሌሎችንም ደግሞ ወደድ!ደግሞም ሌሎችን አስብ! ለሌሎቸም ደግሞ ተጠንቀቅላቸው!ደግሞም ለሌሎቸ መኖር ጀምር! ኢየሱስ መጥቶ የሞተበት ምክንያት ለሌሎች በማሰብ ነው። እኔ እንደ እርሱ መሆን እፈልጋለሁ። እንደ ኢየሱስ መሆን ትፈልጋለህ?

  • ይህ መጽሐፍ የሴት ልጆችን ጉዳት ይፈውሳል! በእዚህ ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረ መጽሐፍ፣ ሴቶች የሚገጥሟቸውን በርካታ አዳጋች ሁኔታዎችን በእግዚአብሔር ጥበብ እርዳታ እንዲያሸንፉ ይነሳሳሉ፡፡ ይህን በተለይ ለሴት ልጆች የተጻፈ ኃይለኛና አዲስ መጽሐፍ ስታነብቢ እግዚአብሔር ሕይወትሽን በመንካት ያበረታሻል፡፡

  • በምድር ላይ የሰው ሕይወት ሰልፍ እንደሆ ታውቃለህን¬? በጦርነት ውስጥ መሆን ብትፈልግም ባትፈልግም ያለንው በጦርነት ውስጥ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር የሰው ሕይወት ብርቱ ሰልፍ ነው ይላል። መልካሙን ገድል እየታገልክ ጦርነቱን ማሸነፍ አለብህ። ይህ ስለውጊያ የሚያስተምረው አዲስ መጽሐፍ መሪዎች በሙሉ ሊያነቡት የሚገባ ነው።

  • ይህ የሚያስደንቅ መጽሐፍ እየሰራ ያለውን መርገም እንድንቋቋም እና ታላቅነትህን እየተዋጋህ ያለውን መርገም ጸጥ ማሰኘት እንድትችል ይረዳሃል። ማንም ብትሆን እግዚአብሔር ላንተ ትልቅ የህይወት ፍጻሜ አለው። የእርግማንን ሃይል ለምቋቋም ይህን መጽሐፍ እንደ ትልቅ መሳሪያ ተጠቀምበት።

  • ክርስቲያን በብዙ አደጋዎች፣ እንቅፋቶችና ወጥመዶች መካከል ነው የሚመላለሰው፡፡ ይህ መጽሐፍ በእኛ ላይ ክፋት ለማድረግ፣ ለመጉዳትና ለማጥፋት አድፍጠው የሚጠባበቁትን በርካታ ስልታዊ አደጋዎችን እንድታይ ዓይኖችህን ይከፍታል። መንፈሳዊ አደጋዎችን በሚመለከት በተጻፈው በዚህ ኃይለኛ መጽሐፍ አማካኝነት ራስህን እርዳ፣ ራስህን አድን ደግሞም ራስህን ነፃ አውጣ!

  • መጋቢዎች መልካም በሆኑ ዜናዎች ምእመኖቻቸውን ለማነቃቃትና ለመመሰጥ ግፊት አለባቸው፡፡ የመስቀሉ መልእክት እስኪጠፋ ድረስ የህዝቡ ግፊት የክርስቶስ ቃል እንዲወሳሰብ ምክንያት ሆኗል፡፡ ዛሬ ክርስቶስን ለ"ማግኘት" "መጐዳት" እንዳለብን ወደሚያሳየን ወደ ክርስትና መሰረት እንመለሳለን፡፡ መሠዋት፣ መከራ መቀበልና ለክርስቶስ መሞትን ስንሰብክ ኃይል ወደ ቤተክርስቲያን ይመለሳል፡፡ ማንም ስኬታማም ሆነ ኃይለኛ የሆነ ሰው የክርስቶስን ቃሎች ኃይል ሊደመስሰው አይችልም፡፡

  • የመጽሐፉ አረስት ህጻን ሆነህ በደስታ የምትዘምረውን መዝሙር ያስታውስሃል.. . መጽሐፍ ቅዱስህን በየቀኑ ታነባለህ? በየቀኑ ትጸልያለህ? ይህ ምጽሐፍ ድንቅ እና ብቸኛ ለሆነው መጽሐፍ ቅዱስ አይኖችህን ይከፍትልሃል። እንዲሁም በየቀንይ መጽሐፍ ቅዱሰን ስታነብና በየቀኑ ስትጸልይ በየቀኑ ወደ አንተ ተአምራቶች እንዲመጡ ይከፍትልሃል። የየቀኑ መጽሐፍ ቅዱስ ንባብህ እና የየቀኑ ጸሎትህ ያስደስትህ!

  • በዚህ ለየት ያለ ምጽሐፍ ውስጥ በልብ የሚጠኑ ቁልፍ የሆኑ የምጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ታገኛለህ። ኢየሱስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በልቡ ይዞ ነበር፤ እኛም ማድረግ አለብን! የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በልብ ለማጥናት እናልም እንዲሁም መልካም እና የትቀየረ ባህሪይ። የክርስቶስ ተከታዮች ነን!

  • ይህ በጌታ የተሰጠ ማረጋገጫ ለዚህ አዲስ እና ኃይለኛ መጽሐፍ “ሰይመው፣ ይገባኛል በል፣ ውሰድ!” መሰረት ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ፣ ቢሾፕ ዳግ ሂዋርድ-ሚልስ አማኙ መንፈሳዊ፣ አካላዊ እና ቁሳዊ መጣስ እንዲሆንለት የሚያስችለውን ዋነኛ ቁልፍ ያሳያሉ፡፡

  • ቅባት ወደ ተሳካ እና ፍፃሜው ያማረ አገልግሎት ውስጥ ለመግባት የሚያስፈልግ ዋነኛ ቁልፍ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች በፍጹም ቅንነት በራሳቸው ጥረት የእግዚአብሔርን ሥራ ለመሥራት ሞክረው መንገድ ቀርተዋል፡፡ እነኚህ ሰዎች ያልተገነዘቡት ነገር “በመንፈሴ (በቅባት) እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም” (ዘካሪያስ 4፡6) የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርህ ነው፡፡ “ይህ ቅባቱን ያዝ” በሚል ርዕስ በቢሾፕ ዳግ ሂዋርድ-ሚልስ የተጻፈ ልዩ መጽሐፍ ቅባቱን መያዝ ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና እንዴት ተደርጐ እንደሚያዝም ተግባራዊ በሆነ መልኩ ያስተምራል ! የዚህን መጽሐፍ ገጾች ስታነብ በውስጥህ ቅባቱን የመያዝ መሻትህ ይቀጣጠል !

  • ከክርስቲያን መሪዎች ውስጥ ታዋቂ የሆነው ዶ/ር ዳግ ሂዋርድ ሚልስ ከሚስጢሮቹ አንዱን እንዲህ በማለት ይናገራል « ማንም ሰው ከእግዚአብሔር ጋር የምታደርገው ህብረት ውስጥ ትልቁ ሚስጢር ምንድ ነው ብሎ ቢጠይቀኝ ፣ካለምንም ጥርጥር የምመልስለት በየቀኑ ከእግዚአብሔር ጋር የማደርገው የጥሞና ጊዜ ኃይል ነው እላለሁ »። ይህን መጽሐፍ ለመጻፍ የወሰነው ፣ አንተም የጥሞናን ጊዜን ኃይል ትርፉን እንድታገኝ በማሰብ ነው።

  • ቤተ ክርስቲያናትን መትከል ካሪዝማቲክ በሆኑ አገልጋዬች ዘንድ በሰፊው የተለመደ ክስተት ነው፡፡ የቀደምት ደቀ መዛሙርት ዋና እንቅስቃሴ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ስኬታማ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ለማካሄድ በርካታ ጭብጦችን ያካተተ ክህሎትን ይጠይቃል፡፡ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ፣ በመላው ዓለም ከ 1200 በላይ አጥቢያዎች ያሏት ቤተ ክርስቲያን መስራችና መጋቢ ሲሆኑ፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተለያዮ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ግብአቶችን ይተነትናሉ፡፡ ይህ መጽሐፍ ቤተ ክርስቲያን መትከልን የሕይወት ግቡ ማድረግ ለሚፈልግ አገልጋይ የስልጠና ማንዋል ነው።

  • ታማኝነት ለመሪዎች የእግዚአብሔር የቅድሚያ መለኪያ ቢሆንም እንኳን ፣በእዚህ ርዕስ የተጻፉ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ በዚህ መጽሐፉ፣ የቤተክርስቲያኖች በመጽናት ማደግን አስመልክቶ በጣም አስፈላጊ መመሪያዎችን በግልፅ ይዘረዝርልናል፡፡ ይህ መጽሐፍ ወቅታዊና ተግባራዊ የሆኑ ርዕሶችን ያካተተ ነው ፣ በመሆኑም ለቤተክርስቲያን መሪዎች የሁልግዜ መገልገያ መሳሪያ ይሆናል፡፡

  • "...ቤቴ እንዲሞላ ወደ መንገድና ወደ ቅጥር ውጣና ይገቡ ዘንድ ግድ በላቸው፤"ሉቃስ 14:23 የእግዚአብሔር የልብ ጩኸት ዓለም እንዲድንና ቤቱ (ቤተ ክርስቲያን) እንድትሞላ ነው! “ትልቅ ቤተ ክርስቲያን” የሚለው ከጋና ትላልቅ ቤተ ክርስቲያኖች የአንዱ መጋቢ የሆኑት የዳግ ሂዋርድ ሚልስ መጽሐፍ የተወለደው ከዚህ መገለጥ ነው፡፡ ይህንን አነሳሽ መጽሐፍ ካነበብክ በኋላ ቤተ ክርስቲያንህ እና አገልግሎትህ ዳግም እንደነበር አይሆንም! “ዶክተር ዳግ ሂዋርድ ሚልስ ለጌታ ለኢየሱስ ክርስቶስ እና ወንጌልን ለዓለም በማዳረስ ውስጥ ላለው ሥራ የተሰጡ ሰው ናቸው፡፡ ታላቅ መሪ እና በአገልግሎት ላሉ ሁሉ አርአያ ናቸው፡፡ እኛም “ቸርች ግሮውዝ

  • ትተውህ የሚሄዱ ሰዎች ሊያጠፉህ ይችላሉ፡፡ ሰዎች ትተውህ በሚሄዱበት ጊዜ ባንተ ላይ የሚመጣብህ መቆዘም፣ ግራ መጋባትና ጭንቀት በቃላት ሊገለፅ አይችልም፡፡ ይህ መጽሐፍ ሰዎች ትተውህ ሲሄዱ ሊያስከትል የሚችለውን ጥፋት እንድትቋቋም የሚረዳህ ነው፡፡ አትሳሳት፡፡ለብቻህ ስትተውና ስትጣል ባንተ አገልግሎት ላይ ብቻ የደረሰ እንዳይመስልህ፡፡ ብዙዎች ይህንን ዓይነት መከራ ተካፍለዋል፡፡ ሰይጣን የመጀመሪያው ዓመፀኛ ነበር ከውድቀቱ ቀን ጀምሮ ብዙ ሰዎች ዓመፀኞች እንዲሆኑ ምክንያት ሆኗል፡፡ ይህን መጽሐፍ በእጅህ ውስጥ በማድረግ ትተውህ በሚሄዱ ሰዎች የሚነሳውን ታማኝ ያለመሆንን መንፈስ ተነስተህ እንድትዋጋው ያደርግሃል፡፡

  • ትእቢት በብዙ አመታቶች ውስጥ የሰውን ዘር ያጠቃ ገዳይ መርዝ ነው። ትእቢት የማይታ ስለሆነ ትልቅ ሽብር ያስነሳል። ይህን አደጋ ልንዋጋው የምንችለው እንዴት ነው? በትህትና ክትባት ነው! ትህትና ዋነኛ መንፈሳዊ መለኪያ ነው። ስለዚህ ደንቅ ነገር ግን መንፈሳዊ መለኪያ ለምጻፍ የደፈሩ ጥቂቶች ናቸው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ ድብቅ የመሰሉት ትእቢት አጋልጠው ያሳዩናል። እንደኛው በትግል ውስጥ በሚኖር ክርስቲያን የተጻፈው ይህ ድንቅ መጽሐፍ እንደ ህጻን አይነት ትህትና የሆነውን የእየሱስ ክርስቶስ ትህትና እንድታሳድግ ያበረታታሃል እንዲሁም ይባርክሃል።

  • አዝመራው ነጥቷል፣ የነፍሳት መከሩም ደርሷል፤ ይሁን እንጂ ወንጌል ሰባኪዎች ወዴት አሉ? ይህ የዳግ ሂዋርድ ሚልስ አነሳሽ መጽሐፍ ክርስቲያኖች ነፍሳትን ማራኪ እንዲሆኑ አስቸኳይ ጥሪ ያደርጋል፡፡

  • ይህ ጥንታዊ የመስጠት ግንዛቤ አይሁዳውያኖችን ወደ ታዋቂ ሐብት ያደረሳቸው ቢሆንም እንኳን ብዙ ሰዎች ከአሥራት መክፈል አስተሳሰብ ጋር ይታገላሉ፡፡ በዚህ መጽሓፍ ውስጥ ቢሾፕ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ አሥራት መክፈል እንዴት አድርጎ ሐብትን ለማፍራትና የብልጽግናን ተአምራት እንደሚያጠንክር ያስተምረናል፡፡ ከዳግ ሂዋርድ ሚልስ ምርጥ ርዕሶች አንዱ በሆነው በዚህ መጽሐፍ ተባረክ፡፡

  • መጽሐፍ ቅዱስ ሁላችንም እንደምናጠፋ ይነግረናል- መጋቢዎችም የተለዩ አይደሉም፡፡ ጥፋቶች ወደኋላ እንጂ ወደፊት እንድንራመድ አያደርጉንም ፡፡አንድም ጥፋት ከስኬትህ ሊያቆምህ ይችላል፡፡ አንድ መጋቢ ሊያጠፋ የሚችለው ነገር ምንድን ነው? የመጋቢዎች አሥሩ ዋና ዋና ስህተቶች ሊሆኑት የሚችሉት ነገሮች ምንድን ናቸው? አደጋ ሊሆኑብህ የሚችሉትን ስህተቶችን እራስህ እንድታይና አንድ መጋቢ ዋና ዋና የሚባሉትን ስህተቶች ከማድረጉ በፊት እንዴት ማስወገድ እንዳለበት የዚህን ድንቅ መጽሐፍ ገፆች እየገለጥክ እንድታነብ ተጋብዘሃል፡፡

  • አብያተ ክርስቲያናት ፍጹም ታማኝ ወዳለመሆን ደረጃ በሚደርሱ ፍጹም አስመሳዮች ተሞልታለች፡፡ ሁል ጊዜም የሰይጣን ዋንኞቹ ቁልፎች ማሳት እና ማስመሰል ናቸው፡፡ አስመሳይ ከሚያደርገው የማስመሰል ጭንብል በስተጀርባ አልፎ ማይት የማይችል መሪ፣ አለማየት ካለመቻሉ የተነሳ ይሰቃያል፡፡ ማስፈራራት፣ መላመድ፣ ግራ መጋባት አገልጋዮችን የሚዋጉ ክፉ መናፍስት ናቸው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ፣ ሰዎች ምን እየተዋጋቸው እንዳለ እንኳን አያውቁም፡፡ ይህ መጽሐፍ ይህንን ለይተህ እንድታውቅና ከውስጥ ያሉትን ጠላቶችህን እንድትዋጋ ይረዳሃል፡፡

  • የወንጌል ስርጭትን ተቃዋሚዎች፣ ምክንያቶች፣ ጥርጣሬና ተናዳጆች ባሉበት ቦታ ሁሉ ውጤታማና ፍሬያማ የሚያደርገውን የዚህን የግድማለት ኃይል ተማረው። የዚህ የዳግ ሂዋርድ ሚልስ መጽሐፍ ከዚህ በፊት ካደረከው በላይ ሰፍሳትን የምታድን ያደርግሃል።

  • ይህ መጽሐፍ ሊያነቡት ግድ ለሚላቸው አገልጋዮች ሁሉ ከዳግ ሂዋርድ-ሚልስ የተገኘ ሌላ ስጦታ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ በአባትና በልጅ መካከል ያሉትን ውስብስብ ግንኙነቶች ስለመወጣት ያሉ ጥያቄዎችን ይመልሳል፡፡ በዚህ መጽሐፍ ትምህርት አማካኝነት እርግማንን ከሕይወትህ አርቀህ በራስህ ላይ በረከትን ታመጣለህ አባቶች መርገምን ከሕይወትህ አርቀህ በረከትን በራስህ ላይ ታመጣለህ፡፡ አባቶች ልጆችንና ተከታዮችን የሚያሳድጉ ልዩ ስዎች ናቸው፡፡ ያለ አባቶች አገልግሎቱን ወደሌላ ትውልድ የሚያሸጋግሩ ልጆች አይኖሩም፡፡ ከአባቶች ጋር ለመቆራኘት ባለህ ችሎታ መሠረት የእግዚአብሔር ጥሪ ወይ ያብባል ወይ ይሞታል፡፡ ይህንን መጽሐፍ በማንበብ

Title

Go to Top