ዳግሂዋርድሚልስ፣በርካታተፈላጊመጽሐፍየጻፉናከእነዚሁምውስጥ“ታማኝነትናታማኝአለመሆን” የተባለውበዓለምላይታዋቂበሆነውንመጽሐፋቸውይታወቃሉ።በአሁኑጊዜዩናይትድዲኖምኔሽንኦርጂኔትድፍሮምዘላይትሃውስግሩፕኦፍቸርች(United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches) ተብሎየሚጠራውቤተክርስቲያንመስራችናቸው፡፡በአሁኑጊዜሶስትሺህቤተክርስቲያኖችአሉት።
ዳግሂዋርድሚልስ፣በዓለማቀፍደረጃወንጌላዊሲሆኑ“ፈዋሹኢየሱስክሩሴድ(HEALING JESUS CRUSADE) ” በተሰኘውእናበአለምዙሪያበተለያዩኮንፈረንሶችላይበአገልግሎታቸውይታወቃሉ፡፡ይበልጥመረጃከፈለጉድህረገጻቸውንይጎብኙ፣www.daghewardmills.org.
-
ቅባት ወደ ተሳካ እና ፍፃሜው ያማረ አገልግሎት ውስጥ ለመግባት የሚያስፈልግ ዋነኛ ቁልፍ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች በፍጹም ቅንነት በራሳቸው ጥረት የእግዚአብሔርን ሥራ ለመሥራት ሞክረው መንገድ ቀርተዋል፡፡ እነኚህ ሰዎች ያልተገነዘቡት ነገር “በመንፈሴ (በቅባት) እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም” (ዘካሪያስ 4፡6) የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርህ ነው፡፡ “ይህ ቅባቱን ያዝ” በሚል ርዕስ በቢሾፕ ዳግ ሂዋርድ-ሚልስ የተጻፈ ልዩ መጽሐፍ ቅባቱን መያዝ ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና እንዴት ተደርጐ እንደሚያዝም ተግባራዊ በሆነ መልኩ ያስተምራል ! የዚህን መጽሐፍ ገጾች ስታነብ በውስጥህ ቅባቱን የመያዝ መሻትህ ይቀጣጠል !
-
ቤተ ክርስቲያናትን መትከል ካሪዝማቲክ በሆኑ አገልጋዬች ዘንድ በሰፊው የተለመደ ክስተት ነው፡፡ የቀደምት ደቀ መዛሙርት ዋና እንቅስቃሴ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ስኬታማ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ለማካሄድ በርካታ ጭብጦችን ያካተተ ክህሎትን ይጠይቃል፡፡ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ፣ በመላው ዓለም ከ 1200 በላይ አጥቢያዎች ያሏት ቤተ ክርስቲያን መስራችና መጋቢ ሲሆኑ፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተለያዮ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ግብአቶችን ይተነትናሉ፡፡ ይህ መጽሐፍ ቤተ ክርስቲያን መትከልን የሕይወት ግቡ ማድረግ ለሚፈልግ አገልጋይ የስልጠና ማንዋል ነው።
-
"...ቤቴ እንዲሞላ ወደ መንገድና ወደ ቅጥር ውጣና ይገቡ ዘንድ ግድ በላቸው፤"ሉቃስ 14:23 የእግዚአብሔር የልብ ጩኸት ዓለም እንዲድንና ቤቱ (ቤተ ክርስቲያን) እንድትሞላ ነው! “ትልቅ ቤተ ክርስቲያን” የሚለው ከጋና ትላልቅ ቤተ ክርስቲያኖች የአንዱ መጋቢ የሆኑት የዳግ ሂዋርድ ሚልስ መጽሐፍ የተወለደው ከዚህ መገለጥ ነው፡፡ ይህንን አነሳሽ መጽሐፍ ካነበብክ በኋላ ቤተ ክርስቲያንህ እና አገልግሎትህ ዳግም እንደነበር አይሆንም! “ዶክተር ዳግ ሂዋርድ ሚልስ ለጌታ ለኢየሱስ ክርስቶስ እና ወንጌልን ለዓለም በማዳረስ ውስጥ ላለው ሥራ የተሰጡ ሰው ናቸው፡፡ ታላቅ መሪ እና በአገልግሎት ላሉ ሁሉ አርአያ ናቸው፡፡ እኛም “ቸርች ግሮውዝ
-
ትተውህ የሚሄዱ ሰዎች ሊያጠፉህ ይችላሉ፡፡ ሰዎች ትተውህ በሚሄዱበት ጊዜ ባንተ ላይ የሚመጣብህ መቆዘም፣ ግራ መጋባትና ጭንቀት በቃላት ሊገለፅ አይችልም፡፡ ይህ መጽሐፍ ሰዎች ትተውህ ሲሄዱ ሊያስከትል የሚችለውን ጥፋት እንድትቋቋም የሚረዳህ ነው፡፡ አትሳሳት፡፡ለብቻህ ስትተውና ስትጣል ባንተ አገልግሎት ላይ ብቻ የደረሰ እንዳይመስልህ፡፡ ብዙዎች ይህንን ዓይነት መከራ ተካፍለዋል፡፡ ሰይጣን የመጀመሪያው ዓመፀኛ ነበር ከውድቀቱ ቀን ጀምሮ ብዙ ሰዎች ዓመፀኞች እንዲሆኑ ምክንያት ሆኗል፡፡ ይህን መጽሐፍ በእጅህ ውስጥ በማድረግ ትተውህ በሚሄዱ ሰዎች የሚነሳውን ታማኝ ያለመሆንን መንፈስ ተነስተህ እንድትዋጋው ያደርግሃል፡፡
-
ትእቢት በብዙ አመታቶች ውስጥ የሰውን ዘር ያጠቃ ገዳይ መርዝ ነው። ትእቢት የማይታ ስለሆነ ትልቅ ሽብር ያስነሳል። ይህን አደጋ ልንዋጋው የምንችለው እንዴት ነው? በትህትና ክትባት ነው! ትህትና ዋነኛ መንፈሳዊ መለኪያ ነው። ስለዚህ ደንቅ ነገር ግን መንፈሳዊ መለኪያ ለምጻፍ የደፈሩ ጥቂቶች ናቸው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ ድብቅ የመሰሉት ትእቢት አጋልጠው ያሳዩናል። እንደኛው በትግል ውስጥ በሚኖር ክርስቲያን የተጻፈው ይህ ድንቅ መጽሐፍ እንደ ህጻን አይነት ትህትና የሆነውን የእየሱስ ክርስቶስ ትህትና እንድታሳድግ ያበረታታሃል እንዲሁም ይባርክሃል።
-
መጽሐፍ ቅዱስ ሁላችንም እንደምናጠፋ ይነግረናል- መጋቢዎችም የተለዩ አይደሉም፡፡ ጥፋቶች ወደኋላ እንጂ ወደፊት እንድንራመድ አያደርጉንም ፡፡አንድም ጥፋት ከስኬትህ ሊያቆምህ ይችላል፡፡ አንድ መጋቢ ሊያጠፋ የሚችለው ነገር ምንድን ነው? የመጋቢዎች አሥሩ ዋና ዋና ስህተቶች ሊሆኑት የሚችሉት ነገሮች ምንድን ናቸው? አደጋ ሊሆኑብህ የሚችሉትን ስህተቶችን እራስህ እንድታይና አንድ መጋቢ ዋና ዋና የሚባሉትን ስህተቶች ከማድረጉ በፊት እንዴት ማስወገድ እንዳለበት የዚህን ድንቅ መጽሐፍ ገፆች እየገለጥክ እንድታነብ ተጋብዘሃል፡፡
-
አብያተ ክርስቲያናት ፍጹም ታማኝ ወዳለመሆን ደረጃ በሚደርሱ ፍጹም አስመሳዮች ተሞልታለች፡፡ ሁል ጊዜም የሰይጣን ዋንኞቹ ቁልፎች ማሳት እና ማስመሰል ናቸው፡፡ አስመሳይ ከሚያደርገው የማስመሰል ጭንብል በስተጀርባ አልፎ ማይት የማይችል መሪ፣ አለማየት ካለመቻሉ የተነሳ ይሰቃያል፡፡ ማስፈራራት፣ መላመድ፣ ግራ መጋባት አገልጋዮችን የሚዋጉ ክፉ መናፍስት ናቸው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ፣ ሰዎች ምን እየተዋጋቸው እንዳለ እንኳን አያውቁም፡፡ ይህ መጽሐፍ ይህንን ለይተህ እንድታውቅና ከውስጥ ያሉትን ጠላቶችህን እንድትዋጋ ይረዳሃል፡፡
-
ይህ መጽሐፍ ሊያነቡት ግድ ለሚላቸው አገልጋዮች ሁሉ ከዳግ ሂዋርድ-ሚልስ የተገኘ ሌላ ስጦታ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ በአባትና በልጅ መካከል ያሉትን ውስብስብ ግንኙነቶች ስለመወጣት ያሉ ጥያቄዎችን ይመልሳል፡፡ በዚህ መጽሐፍ ትምህርት አማካኝነት እርግማንን ከሕይወትህ አርቀህ በራስህ ላይ በረከትን ታመጣለህ አባቶች መርገምን ከሕይወትህ አርቀህ በረከትን በራስህ ላይ ታመጣለህ፡፡ አባቶች ልጆችንና ተከታዮችን የሚያሳድጉ ልዩ ስዎች ናቸው፡፡ ያለ አባቶች አገልግሎቱን ወደሌላ ትውልድ የሚያሸጋግሩ ልጆች አይኖሩም፡፡ ከአባቶች ጋር ለመቆራኘት ባለህ ችሎታ መሠረት የእግዚአብሔር ጥሪ ወይ ያብባል ወይ ይሞታል፡፡ ይህንን መጽሐፍ በማንበብ
-
እረኛ የሚለውን ቃል ስንሰማ በሃሳባችን የሚመጣው « በግ « ነው። በጎች በእረኞች የሚያስፈልጋቸው ጥገኛ የሆኑ ፍጡሮች ናቸው። እረኛ በጎችን የሚንከባከብና የሚወድ እነርሱንም የሚመራ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር እኛ የእርሱ የማሰማርያው በጎችን እንደሆንን ያሳየናል። ኢየሱስ ደቀመዝሙሩን ጴጥሮስን ለጌታ ፍቅር ማረጋገጫ እንዲሆን በጎቼን መግብልኝ ብሎታል። እረኛ መሆን ትልቅ ሥራ ነው። በእግዚአብሔር ግብረኃይል ውስጥ በመካተት በጎችን መጠበቅ ትልቅ መታደል ነው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ የእግዚአብሔርን ህዝብ የመጠበቅ ታላቅ ሥራ ውስጥ እንዴት አድርገን መግባት እንዳለብን ይጋብዘናል፣ይገፋፋናል፣ያሳየናል። ካማረው
-
እግዚአብሔርን ማገልገል ትልቅ ነገር እንደሆን ሰምተህ ልታውቅ ትችላለህ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ማገልገል እንዴት ትልቅ ነገር እንደሆነ ጠለቅ ብልህ አስበህ ላታውቅ ትችላለህ። በዚህ ለየት ባልው የዳግ ሂዋርድ ሚልስ መጽሕፍ ውስጥ ማን የእግዚአብሔር አግልጋይ እንደሆነ እና እንዴት እግዚአብሔርን ማገልገል እንዳለብህ ትረዳለህ። እግዚአብሔርን ብሚያገለግሉት እና እግዚአብሔርን በማያገልግሉት መካክል ያልው ልዩነት ግልጽ ባለው መንገድ ይብራልህ! እግዚአብሔርን ክሚያገለግሉት ውስጥ የምትቆጠር ሁን!